የአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ እና ሌሎች ሶስት ሀገራት የምግብ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።
የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ለኢትዮጵያ ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ሀይቲና ጅቡቲ 52ሚሊየን ዶላር የምግብ እርዳታ በተባበሩት መንግስታት በኩል ልኬያለሁ ብሏል።
ድጋፉም በሀገራቱ ምግብ ለተቸገሩ 1.9 ሚሊየን ሰዎች ይውላል ብሏል።
መግለጫው ዛሬም ቀዳሚ ለጋሽ አሜሪካ ናት ያለ ሲሆን ገንዘቡን ብናሰላው ለአንድ ሀገር 13ሚሊየን ዶላር ወይም 1.7ቢሊየን ብር ብቻ ነው።
የምግብ ዋስትና ማሳካት የሉዓላዊነት ቀዳሚ መገለጫ መሆኑን ቅዳሜ ገበያ ታምናለች።