የነፍስ ኄር ቤተልሔም ተስፋዬን ለማስታወስ፣ በሕይወት ዘመኗ የተወችውን አሻራና በቤተሰቦቿ፣ በወዳጅ ዘመዶቿ እና በአድናቂዎቿ ልብ ውስጥ ያላትን ልዩ ስፍራ ለመዘከር የመታሰቢያና የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።
በሥነ ሥርዓቱ የመክፈቻ ጸሎት፣ የመጽናኛ መልዕክት፣ መዝሙር፣ የቤተሰቦቿና የጓደኞቿ የትዝታ ምስክርነት እንዲሁም የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት ተካትተዋል።
ተሳታፊዎቹ ሻማ በማብራት ለቤተልሔም ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት የገለጹ ሲሆን፣ ከእሷ ጋር ያሳለፏቸውን ውድ ጊዜያትና የማይረሱ ትዝታዎችንም አጋርተዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ሰው በአካል ቢለይም በመልካም ሥራው፣ በፍቅሩና በትዝታው ሕያው ሆኖ እንደሚቀጥል ተገልጿል። ለቤተሰቦቿና ለወዳጅ ዘመዶቿም የመጽናናት መልዕክት ተላልፏል
