የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስከሬን ከመኖሪያ ቤታቸው ፒያሳ ወደ ሚገኘው (በኒ) መስጅድ ሽኝት እየተደረገለት ነው።
የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስከሬን ላንቻ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ለ40 ዓመታት በማስተማር ወዳገለገሉበት ኑር መስጅድ ነው እያቀና የሚገኘው፡፡
በሽኝት መርሐ ግብሩ ኡለማዎች፣ ደረሳዎች፣ ኡስታዞች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል፡፡
በቀጣይ በኑር መስጅድ ሰላተል ጀናዛ ከተሰገደ በኋላ በሚሊኒዬም አዳራሽ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት ሽኝት ይደረጋል፡፡
ከቀኑ 10 ሰዓት ላይም ሥርዓተ ቀብራቸው የሚፈጸም መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አስታውቋል፡፡