የትግራይ ኃይል አባላት ሰልፈኞች ለአራተኛ ቀን የመኪና መንገድ ዘግተዋል

Date:

ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም የትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዋና ከተማ ወደ ሆነችው የዓዲግራት ከተማ የሚያስገቡና የሚያስወጡ ሶስት ዋና መንገዶች ተዘግተዋል።

ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ከዓድዋ ወደ ዓዲግራት ሲጓዝ ሴሮ በተባለ ቦታ መንገድ ተዘግቶበት ከሰዓት በኃላ ተከፎቶ ወደ ከተማዋ የተጓዘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል እንዳረጋገጠው ፤ ከዓዲግራት ወደ መቐለ ዓድዋና ዛላአንበሳ አቅጣጫ የሚያመሩ መንገዶች ተዘግተዋል።

ከጥቅምት 3/2018 ዓ.ም ወዲህ ከክልሉ ምስራቃዊ ፣ ደቡባዊ ዞኖች ወደ መቐለ የሚወስዱ መንገዶች በኣጉላዕና ፣ በመኾኒ ወደ እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ የሚወስድ መንገድ በእንዳባጉና ከዓድዋ ወደ ዓዲግራት የሚወስድ በሴሮ ተዘግተው በዚያው ቀን በተለያዩ ሰዓቶች መከፈታቸው ይታወሳል።

የክልሉ ካቢኔ በመንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ በኩል ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፤ የሰራዊቱ አባላት ያነሱት የደመወዝ ጭማሪ  የጥቅማ ጥቅምና የመሬት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል መመሪያ ማውጣቱን ትላንት አሳውቆ ነበር። ያም ቢሆን ግን ዛሬም መንገዶች ተዘግተዋል።

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

‹‹ኢሳያስ አፈወርቂ ከአገር ይኮበልላሉ››

የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር ሻብያን ነክሰው ይዘዋል፡፡ ዛሬ ደግሞ፣ ፕሬዝዳንት...

የቀድሞው የዶናልድ ትራምፕ አማካሪ ጆን ቦልተን ተከሰሱ

ጆን ቦልተን በሪፐብሊካኑ የመጀመሪያው ዙር የፕሬዚዳንትነት ወቅት የብሄራዊ ደህንነት...

“ወደራስ መመለስ!”

በ99ኛ የስብሐቲዝም መድረክ ከፍልስፍና መምህሩና ጋዜጠኛ ደረጀ ይመር ጋር...