የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ለ100 ሴቶች ነፃ የጡትና የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ ዕድል ፈጠረ

Date:

የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የጥቅምት ወር ዓለም አቀፍ የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ምክንያት በማድረግ ለ100  ሴቶች ነፃ የጡት እና የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ ዕድል መፍጠሩን አስታውቋል ።

ሆስፒታሉ ይህንን ያስታወቀው  ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም ላይ ከየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ጋር በመተባበር የጡት እና የማህፀን በር ካንሰር በሽታን መከላከልን አስመልክቶ ለማህበረሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን ባከናወነበት ወቅት ነው ።

የሆስፒታሉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ የአካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ስንታየሁ ድንቁ እንደገለፁት፡ ሆስፒታሉ ለአንድ ቀን ብቻ ነፃ የምርመራ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ።

ሆስፒታሉ ለአንድ ቀን ብቻ በሚሰጠው ነፃ ምርመራ ለ100 ሴቶች ነፃ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ምቹ ዕድል ቢፈጥርም በግንዛቤ እጥረት ችግር ምክንያት ምርመራ እያደረጉ ያሉት ውስን መሆናቸውን ተናግረዋል ።

ሆስፒታሉ ይህንን አገልግሎት እየሰጠ ያለው ከየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ጋር በመሆን እንደሆነ የገለፁት ስራ አስፈፃሚዋ በቀጣይ በጡት እና በማህፀን በር ካንሰር ላይ ያለውን የግንዛቤ እጥረት ለመፍታት ወጥነት ያለው አሰራር መዘርጋት ያስፈልጋል ብለዋል ።

በተለይም የችግሩን አስከፊነት በመረዳት ማህበረሰቡ አከባቢው ቀረብ ባለ ሆስፒታል በመሄድና ምርመራ በማድረግ የጡት ሆነ የማህፀን በር ካንሰርን ምርመራ ማድረግ ይኖርበታል ሲሉ ጠቁመዋል ።

(አሐዱ ሬድዮ)

 

 

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ቢል ጌትስ ስለ AI አጠቃቀማችን ምን አሉ?

የማይክሮሶፍት መስራች ቢል ጌትስ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና ሮቦቶች...

ዲቪ ሎተሪ 2027 ዳግም እንዳይከፈት በፍርድ ቤት ታገደ

የአሜሪካ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የዲቪ ሎተሪ 2027 ምዝገባ...

የማይደበዝዝ የታሪክ አሻራ፤

አበበ ቢቂላና ማሞ ወልዴ በዓለም መድረክ ግዮን መጽሔት :-...

በብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ለስድስት ወር በደብረ ሊባኖስ ገዳም እንዲቆዩ ተወሰነ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ...