የዓለም የወርቅ ዋጋ ለመጀመሪያ ጊዜ 5,100 ዶላር በማለፍ አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

Date:

በዓለም አቀፍ ደረጃ እየታየ ያለው ጂኦፖለቲካዊ አለመረጋጋት ባለሀብቶች የወርቅ ክምችታቸውን እንዲያሳድጉ በማድረጉ፣ የአንድ አውንስ ወርቅ ዋጋ ለመጀመሪያ ጊዜ 5,100 ዶላር በማለፍ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።

ሰኞ ጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም በዓለም ገበያ የአንድ አውንስ ወርቅ ዋጋ 2.2 በመቶ ጭማሪ በማሳየት 5,110.50 ዶላር ደርሷል።

የወርቅ ዋጋ እ.አ.አ በ2025 ብቻ የ64 በመቶ እድገት ያሳየ ሲሆን፣ ይህም ከ1979 ወዲህ የታየ ከፍተኛው ዓመታዊ ጭማሪ መሆኑ ተገልጿል።

ለዚህም እንደ ዋና ምክንያት የተጠቀሱት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በተለያዩ ሀገራት ላይ የጣሉት ከፍተኛ የታሪፍ ማዕቀብና እየተፋፋመ የመጣው የንግድ ጦርነት የፈጠረው ስጋት ነው።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በካናዳ፣ በፈረንሳይና በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ላይ እስከ 200 በመቶ የሚደርስ የታሪፍ ማዕቀብ እንደሚጥሉ መዝታቸው በዓለም አቀፍ የንግድ ሰንሰለት ላይ መስተጓጎል ፈጥሯል።

ይህ ሁኔታ ባለሀብቶች ይበልጥ አስተማማኝ ወደሆነው የወርቅ ኢንቨስትመንት እንዲሸሹ ያደረገ ሲሆን፣ የዶላር የመግዛት አቅም መዳከምም ወርቅ በሌሎች ሀገራት ገንዘቦች ይበልጥ ተመራጭ እንዲሆን አድርጎታል።

ከወርቅ በተጨማሪ የብር ዋጋም በተመሳሳይ ሁኔታ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቶ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውንስ 100 ዶላር መሻገሩ በዘገባው ተመላክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጠ/ሚ ዐቢይ ከተለያዩ የዓለም መሪዎች ጋር በCOP32 ዝግጅትና ትብብር ዙሪያ ተወያዩ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቱርክ አንታሊያ በተካሄደው COP31...

ዲጂታል ፈጣሪዎች ግብር ይከፍላሉ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፌዴራል የገቢ ግብር ደንብን ለማሻሻል ያወጣው...

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...