በባንክ ኦፍ አሜሪካ አቅራቢነት እሁድ ኅዳር 13 ቀን 2019 ዓ.ም በሚካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚሳተፉ ታዋቂ አትሌቶች ዝርዝር ይፋ ሆኗል።
በወንዶች ምድብ የያለፈው ዓመት አሸናፊ ይስማው ድሉ፣ ቢኒያም መላክ፣ ይበልጣል ጋሻሁንና ኃይለማርያም አማረ ከዩጋንዳዊው ሊዮናርድ ክዌሪት፣ ኬንያዊው ኬልቪን ሲጌይና ታንዛኒያዊው ፌድሪክ ፋውስቲን ጋር ይፎካከራሉ። ይስማው ድሉ የውድድሩን የቦታ ክብረወሰን ለመስበር 10 ሰከንድ ብቻ የቀረው አትሌት ነው።
በሴቶች ምድብ የ2025 የቢስሌት ጌምስ አሸናፊና የ2024 የታላቁ ሩጫ ሁለተኛ የነበረችው የኔዋ ንብረት ከበርነሽ ደሴና የዓለም የወጣቶች 3 ኪሎ ሜትር መሰናክል ሻምፒዮን አልማዝ ዮሐንስ ጋር ጠንካራ ፉክክር ይጠበቃል።
ውድድሩ በዓለም አትሌቲክስ የዩቲዩብ ቻናል በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ ሲሆን፣ ከዋናው ውድድር በፊት ቅዳሜ ኅዳር 12 ቀን የእንጦጦ የ3 ኪሎ ሜትር ሩጫና በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የህጻናት ሩጫ ይካሄዳሉ።
