ጠ/ሚ ዐቢይ ከአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ከአሜሪካ አፍሪካ እዝ አዛዥ ጄነራል ጋር ተወያዩ

Date:

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ቲ ላንዳው እና የአሜሪካ አፍሪካ እዝ አዛዥ ጄነራል ዳግቪን አንደርሰን ጋር በጽሕፈት ቤታቸው መወያየታቸውን አስታወቁ።

ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸውን ባሰፈሩት መልዕክት “በጽሕፈት ቤታችን ከተገኙት ቲ ላንዳው እና ከጄነራል ዳግቪን አንደርሰን ጋር ተወያይተናል” ብለዋል። አክለውም ቀጣይነት ያለው ትብብር እና መከባበርን አፅንዖት ለሰጠው ደማቅ እና ገንቢ ውይይታችን ምስጋናዬን አቀርባለሁ ሲሉ ገልጸዋል።

በተጨማሪም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ክሪስቶፈር ላንዳውን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መምከራቸውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች የጋራ ፍላጎት ባላቸው ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሐሳብ ልውውጥ አድርገዋል ተብሏል።

በትላንትናው ዕለት ኢትዮጵያ የገቡት የአሜሪካ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፎር ላንዳው እና የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን በኢትዮጵያ አየር ኃይል በቢሾፍቱ የተዘጋጀውን ዓለም አቀፍ የአቭዬሽን ኤክስፖ ጎብኝተዋል።

ክርስቶፎር ላንዳው ከጉብኝቱ በኋላ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀበባል ምስጋና አቅርበው፤ ኢትዮጵያ በመገኘታቸው ክብር እንደሚሠማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል ያለው ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጠልም ተናግረዋል።

የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን በበኩላቸው ለቀጠናው ሰላም በተለይም እንደ አልሸባብ እና አይኤስኤስ ያሉ ሽብረተኞችን ለመከላከል እና ለመደምሰስ በጋራ እንሰራለን ማለታቸውን መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል።

ክርስቶፎር ላንዳው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በ #ግብጽ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው። ይህ ጉብኝት ከዛሬ ጥር 16 እስከ ጥር 24 ቀን 2018 ዓ.ም በምስራቅ አፍሪካ የሚያደርጉት ጉብኝት አካል ሲሆን ሚኒስትሩ በቀጣይ በኬንያ እና ጅቡቲ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...