የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የሕወሓት ሠራዊት የሚባል ነገር እንደሌለና ሕወሓትም ሠራዊት ሊኖረው እንደማይችል ትላንት ምሽት ለኢዜአ በሠጡት ቃለ ምልልስ ላይ ተናግረዋል።
አቶ ጌታቸው፣ ሕወሓት ‘የምመራው ሠራዊት አለኝ’ ማለቱ ተቀባይነት እንደሌለውም ገልጸዋል።
ሕወሓት ለ50 ዓመታት ባንድ ቦታ ላይ ተቸንክሮ የቀረና በሌሎች መስዋዕትነት ኅልውናውን ለማስቀጠል የሚፈልግ ድርጅት ነው ሲሉ የተቹት አቶ ጌታቸው፤”የዚህ ድርጅት አባል ሆኖ መቀጠል በራሱ አስቀያሚ ነገር ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
በትላንትናው ምሽት ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር የፌደራል መንግሥቱን ወክለው የፕሪቶሪያውን ስምምነት የተደራደሩት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንም ከኢዜአ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡፡
