ሮብሎክስ ስለሚባለው “ጌም” (ማስጠንቀቂያ ለወላጆች)

Date:

(ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)


ልጆች ያሏችሁ ወላጆች Roblo*x ስለሚባል Game አታውቁም ብዬ አልገምትም። ቢያንስ ስሙን ሳትሰሙት አልቀራችሁም። ጨዋታው ሕጻናትም አዋቂዎችም የሚጫወቱበት ነው::

በየቀኑ ከ40ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ገብተው ይጫወቱበታል። ሌሎችም እጅግ በጣም ብዙ ጌሞች አሉ። ሮብሎክስ ትልቅ መወያያ የሆነው ጌሙ ጸረ ሕጻናት የሆኑ እና ሕጻናት የሚያጠምዱ ሰዎች ዋነኛ መናኸሪያ በመሆኑ ነው።

የትኛውም ሕጻናት የሚጠቀሙት ቴክኖሎጂ የቤተሰብ መቆጣጠሪያ (parental control) እና የዕድሜ ገደብ ይኖረዋል። ለምሳሌ Youtube ለልጆች ስንሰጥ ማየት ያለባቸውን በዕድሜ መገደብ እና ሌላውን መዝጋት እንችላለን።

የሕጻናት ዩቲዩብ የሚባልም ራሱን የቻለ ለብቻው አለ። ባይኖርም እንኳን ያንኑ ያለውን የትልልቆቹን ለሕጻናት በሚሆን መልክ መገደብ የሚያስችል ክፍል አለው። ባለሙያዎችም ይህንን ያረጋግጣሉ።

በሌላ በኩል ሮብሎክስ ይህንን ያደረገ ቢመስልም ከሌሎቹ ጌሞች በተለየ ሁኔታ የቤተሰብ መቆጣጠሪያ (parental control) እና የዕድሜ ገደቡ የይምሰል እንጂ የማይሠራ መሆኑን የሳይበር ሴኪዩሪቲ ባለሙያዎች እየገለጹ ነው።

ይህም ማለት የ 8 እና የ9 ዓመት ሕጻናት አዋቂዎች ማየት የሌለባቸውን በጌም መልክ የተዘጋጁ መጥፎ ነገሮች ያያሉ ማለት ነው:: ከዚያም አልፎ በውስጥ መስመር ሕጻናት እየመሰሉ ቀርበው የሚያባብሏቸውና ልባቸውን አሸፍተው ከቤት የሚያስኮበልሏቸው አጥማጆች ሰለባ ይሆናሉ። እጅግ ብዙ ልጆች በዚህ መልክ ጠፍተው ቀርተዋል።

ሮብሎክስ ይህንን መቆጣጠር ሲችል የማያደርገው ችሎታና ባለሙያ አጥቶ ሳይሆን ዋነኛ ተጠቃሚዎቹ ሕጻናትን በማበላሽት ላይ የተሰማሩ ሰዎች እና በዚሁ ወንጀል ላይ የተሰማሩ ቡድኖች በመሆናቸው ነው። ዝርዝሩ ብዙ ነው።

ለማንኛውም ልጆቻችሁ ይህንን ጌም የሚጫወቱ ወላጆች ጨክናችሁ አስወጧቸው። ልጆቹ ጨዋታውን ከመልመዳቸው እና ከመውደዳቸው የተነሣ ብዙ ልቅሶ፣ ጫጫታ፣ ተቃውሞ ቢገጥማችሁም ቻሉት። ስልክ እና ታብሌት ካለ አፑን አጥፉት።

በኮምፒውተርም ቢሆን በቀጥታ ያለ አፕ/APP እንዳደጫወቱ ተጠንቅቃችሁ አጥፉ። የሙያ ድጋፍ ሲያስፈልግ የሚያውቁ ወዳጆቻችሁን ለመጠየቅ ወደ ኋላ አትበሉ። የልጆቹ ዕድሜ 18 በላይ ሆኖ ራሴንችያለሁ ማንም አያዘኝም እስካላሉ ድረስ ለየትኛውም ልጅ ይህንን ጌም እንዲጫወት አይመከርም።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ቃል አቀባይዋ ዩክሬን የአፍሪካ ሀገራትን መበቀል ትፈልጋለች አሉ

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፣ ኪዬቭ የአፍሪካ አገራት...

ሕጻኑ በሀገሪቱ የመጀመሪያ በሆነ ቀዶ ሕክምና ተወለደ

የ28 ዓመቷ ወይዘሮ ሰናይት ታምራት ቀደም ሲል በነበረው እርግዝናዋ...

ግብፅ የኤርትራን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እንዲከበር ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች

የግብፅ ፕሬዝዳንት አብድል ፈታህ አልሲሲ፤ የኤርትራን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት...