ትራምፕ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ለሚፈጸሙ ግድያዎች የሞት ቅጣት እንዲፈረድ ጠየቁ

Date:

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ሰው በመግደል የሚከሰሱ ግለሰቦች የሞት ቅጣት እንዲወሰንባቸው ለመጠየቅ ማቀዳቸውን ተናገሩ።

ትራምፕ በዋይት ሐውስ በተካሄደ የካቢኔ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የሞት ቅጣት ይህንን ዓይነቱን ወንጀል “የሚያስቀር” እርምጃ ይሆናል ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ፤ በከተማዋ አሉ ያሉትን “ሙሉ እና አጠቃላይ ሕግ አልባነት” ለመዋጋት በመቶዎች የሚቆጠሩ የብሔራዊ ዘብ እና የፌዴራል ሕግ አስከባሪ መኮንኖች በአሜሪካ ዋና ከተማ አሰማርተዋል።

እርምጃው በቺካጎ እና በሌሎች ከተሞች ሊደገም እንደሚችልም ጠቁመዋል፥።

የዋሽንግተን ከንቲባ ሙሪየል ቦውሰር፤ ከ2023 ወዲህ በከተማዋ የሚፈጸመው የወንጀል መጠን መቀነሱን በመጥቀስ ፕሬዝዳንቱ ስለሚፈጸመው ወንጀል ያቀረቡትን ክስ ውድቅ አድርገዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...