ሲኒማቶግራፊ (Cinematography)

Date:

ክፍል 1

ሰላም ውድ የግዮን መጽሔት አንባቢያን፣ እንዴት ናችሁ? ለአንድ ዓመት የመረጃ እና የእውቀት ሙዳይዋን ለአንባቢያን እንዳታደርስ ታግዳ የነበረችው መጽሔታችን ወደ ሥራዋ ተመልሳለች፡፡ ደስ ብሎናል ፤ እንኳን ደስ አላችሁ፡፡ ‹‹ሲኒማቶግራፊ›› በሚል ጽንሠ ሐሳብ አጠቃላይ የፊልም አሠራርን ከስክሪፕት አፃፃፍ እስከ ኤዲቲንግ የፊልም ጥበብን ለእናንተ እንካችሁ ሊል እነሆ ዛሬ በክፍል አንድ ጀምሯል፡፡ በቅድሚያ ንባበ ቃላቱን በማፍታታት እንጀምር፡-

Cinematography፡- የግሪክ ቃል ሲሆን ‹‹kinema›› እንቅስቃሴ፣ ‹‹graphein›› መቅረፅ በአንድ ላይ ሀሳቡ እንቅስቃሴ ያለው ምስልን መፍጠር እንደማለት ነው፡፡

Videography፡- ይህም ከሁለት የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን፣ ‹‹video›› ማለት ኤሌክትሪካል ሲግናል graphein (witing or record) እንቅስቃሴ ያለው ምስልን ወደ ቪዲዮ ቴፕ፣ ዲስክ ሪኮርደር አሊያም ወደ ሚሞሪ ካርድ convert አርገን ዳታ የምንይዝበት ሂደትን ቪዲኦግራፊ እንለዋለን፡፡

video recording፡- የምስል እና የድምፅን ኢንፎርሜሽን የምንይዝበት ሂደት ነው፡ በቀደመው ግዜ የቴቪዥንም ሆነ የሬዲዮ ስርጭት ይተላለፍ የነበረው ስቱዲዮ ውስጥ የሚቀረፀው ምንም ኤዲት ሳይደረግ በቀጥታ የአየር ሞገድ በየቤቱ እንዲደርስ ተደርጎ ነበር፡፡ አቅራቢው ሳል ቢይዘው ቢያስነጥስ ሌላም ሌላም ድምፆች ቢያጋጥሙ ሁሉም በአድማጩም ሆነ በተመልካቹ ይሰማል፡፡ ሌላው በጣም የሚያሳዝነው ኤሌክትሮኒካል ዲቫይዝ ሪኮርደር ስላልነበር የሚተላለፈውን ፕሮግራም በድጋሚ ማስተላለፍም ሆነ ለታሪከ ማስቀመጥ አይቻልም ነበር፡፡ በግዜው የነበረው ብቸኛ አማራጭ ለቲቪ የሚሆን እንቅስቃሴ ያለው ምስል በፊልም ካሜራ ይቀረፅና telecine ተጠቅመው ፊልሙን ወደ ቪዲዮ ቀይረው ያስተላልፉታል፡፡ አሁን ግን በጣም ብዙ ቪዲዮ ሪከርድ ማረጊያ ዲቫይዞች ስለተፈጠሩ ምስልም ድምፅም (camcorder) በአንድ ላይ ይቀርፃሉ፡፡

Three TV systems

1. NTSC (NATIONAL TELEVISHION STANDARD COMMITTEE) ከለር ሲስተም ይጠቀማሉ፡፡ USA, CANADA, MEXICO, JAPAN የመሳሰሉ ሀገራት ይጠቀሙታል   525 resolution አለው፡፡ resolution ማለት የካሜራ pixel ጥራት መለኪያ ነው፡፡ NTSC ቲቪ ሲስተም በሰከንድ 30 ፍሬም የተነሱ ፒክቸሮችን ብቻ ይቀበላል፡፡

2. PAL (PHASE ALTERNATION  LINE)  ከለር ሲስተም ነው፡፡  በዚህ ሲስተም የሚጠቀሙት  Ethiopia, England, አብዛኛው የአፍሪካ እና የአውሮፓ ሀገራት፡፡ resolution 625 በሰከንድ 25 ፍሬም፡፡

3. SECAM (SEQUENTIAL COLOR A MEMORY) ከለር ሲስተም ይጠቀማሉ፡፡ ከPAL ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ ሩሲያ እና አንድ አንድ የአውሮፓ ሀገራት በዚህ ሲስተም ይጠቀማሉ፡፡ resolution 625 በሰከንድ 25 ፍሬም፡፡

በሰከንድ 25 ፍሬም ማለት ቪዲዮ ሪከርድ የምናረግበት ካሜራ በሰከንድ 25 ፎቶዎችን አንስቶ ሲቀጣጥለው ነው ቪዲዮ ወይም ተንቀሳቃሽ ምስል ተፈጠረ የምንለው፡፡ ይሄ ማለት ለNTSC የተቀረጸ ቪዲዮን PAL ሲስተም ላይ እናጫውተው ብንል አይሰራም፡፡ ምክንያቱም frame rate ይለያያል፡፡ 30 እና 25 ፍሬም በሰከንድ capture ስለሚያደርግ፡፡ በነገራችን ላይ ቪዲዮ የሚባል ኮንሰፕት እስካሁን የለም ካሜራዎች ከላይ እንደጠቀስኩት በሰከንድ 25 እና 30 ፎቶዎችን capture ያደርጉና እየቀጣጠሉ ምስሉን ወደ እንቅስቃሴ ይቀይሩታል እንጂ በቀጥታ ቪዲዮ የሚቀርፅ ካሜራ እስካሁን አልተፈጠረም፡፡  

ዘመናዊ የቪዲዮ ካሜራዎች ከ2010 ጀምሮ ለ digital cinematography እድገት ጉልህ አስተዋፅዋ አበርክተዋል፡፡ በዝቅተኛ በጀት ጥራት ያለው ፕሮዳክሽን እንዲኖር አድርገዋል፡፡ እነሱም፡-

1. Arii alexa             .    

 2. Red digital cinema        

3. balck magic                                     .                        4. Canon cinema EOS     

5. Panavision genesis   

በ Arii alexa የተቀረፁ ተወዳጅ ፊልሞች፡- mission impossible, rough nation, captain America, allegiant.

የተንቀሳቃሽ ምስል ታሪካዊ አመጣጥ

የመጀመሪያው ፎቶ ግራፍ ማንሻ አርቴክቸራል ፎቶ ግራፍ ማሽን የተፈጠረው በ1830ዎቹ ፈረንሳይ ውስጥ በጆሴፍ ኔምፊስ እና በጓደኛው ዲጎራ ነበር፡፡ አንድ ፎቶ ለማንሳት 10 ሰዓት ይፈጃል፡፡ ከዛ ግን ማሽኑ ሴቭ ስለማያደርግ ምስሉ ይጠፋል ፤ በጣም አድካሚ እና አሰልቺ ነበር፡፡

ከዛ በመቀጠል እነ ጆሴፍ የሰሩትን አርቴክቸራል ፎቶ ግራፍ ቶማስ ኤልቫ ኤዲሰን እና ዊሊያም ዲክሰን በ1870ዎቹ አካባቢ ፎቶውን ጨለማ ውስጥ ከተው ከፊት ብርሀን ሲበራበት ፎቶውን የሚያንቀሳቅስ zoetrope የተባለ ማሽን ሰሩ፡፡ ልክ የዚህ አይነት ዞይትሮፕ ተንቀሳቃሽ ምስል ጄኪ ቻን እና የእውቁ አሜሪካዊ አክተር ዊል ስሚዝ ልጅ ጃደን ስሚዝ የሚሰሩበት ‹‹the karate kid›› የተሰኘ ፊልም መግቢያ ላይ እናገኛለን፡፡

ከዛም በድጋሚ ሁለቱ የቴክኖሎጂው ፈጣሪዎች ኤዲሰን እና ዊሊያም በ1890 በሰከንድ 12 ምስል የሚያነሳ kinetography የተባለ መሳሪያ ፈለሰፉ፡፡

ከ1895 በኋላ ግን ታሪክ ተቀየረ፡፡ አጉስት እና ሉዊስ የተባሉ ሁለት ወንድማማቾች (ሉሚየር ብራዘርስ) ሲኒማቶግራፊ የሚለውን ሐሳብ ለአለማችን አስተዋወቁ፡፡ የአባታቸው ሉሚየር ፎቶ ቤት ውስጥ ለአመታት ተመራምረው 16 ፎቶ በሰከንድ የሚያነሳ መሳሪያ ፈጠሩ፡፡ በሰሩት ቪዲዮ ሪከርደርም ህፃናት ምግብ ሲበሉ፤ የውሀ ፍሳሽ ፏፏቴ፤ ሰራተኞች ከፋብሪካ ከስራ ሲወጡ ይህን የመሳሰሉትን ቪዲዮዎች ለ20 እና ለ25 ደቂቃ በመቅረፅ ለአለማችን የመጀመሪያውን ቪዲዮ /ተንቀሳቃሽ ምስል/ እውን አደረጉት፡፡ ይህንንም ቪዲዮ ልከ አሁን ገንዘብ ከፍለን ሲኒማ ገብተን ፊልም እንደምናየው አነሱም ብር እያስከፈሉ ለ5 አመት አሳዩት፡፡ ከግዜ በኋላ ግን ተመልካቹ መሰልቸት ጀመረ፡፡ ይሄ የቀን ተቀን ሕይወቴ ነው ወደ ፋብሪካ ስገባ እና ስወጣ የተቀረፀን ምስል ከፍዬ ማየቴ ምንድን ነው ጥቅሙ ብሎ ማየቱን አቆመ፡፡ ሉሚየር ብራዘሮች ይሄን ሲያዩ ይሄ ቴክኖሎጂ ተስፋ የለውም የትም አይደርስም አሉ፡፡ ሲኒማቶግራፊን እራሳቸው ፈጥረው እራሳቸው ሊቀብሩት ነበር፡፡ ሲኒማቶግራፊ አሁን ያለበትን እድገት አንዴ ተነስተው ቢያዩ ምን ይሉ ይሆን?  CGI ኮምፒውተር ጀነሬቲንግ ኢሜጅ ከሲኒማው አለም ፈንገጥ ያሉ ሳይንቲፊክ ፊልሞችን እያሳየን ነው ለምሳሌ፡-

– Spider man (3)  2007  – Avator  (2009)

– District 9  (2009)      – transformer (2007)

– Tron  (1982)          – Gladiator (2000)

– The matrix (1999)       – The last star fight (1984) የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡ 

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ መልክ የሚያሳዩ የአደባባይ ሐውልቶች

በኢትዮጵያ በተለይም በመዲናዋ ውስጥ የታሪክ ምዕራፎችን በአደባባይ ቆመው የሚያስመለክቱ፣...

እድሜያቸው 12 እና 13 የሆኑ ህፃናት በስኳር በሽታ ኩላሊታቸው እንዳይሰራ እየሆነ ነው

ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች የሚያጋልጡ የታሸጉ ምግቦችን ለመቆጣጠር የሚያስችል አዋጅ...

ከፍተኛ ተወዳዳሪነት በታየበት ጨረታ አሸናፊዎች ውል እንዲፈፅሙ ተጠየቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በከተማው...

ሰማያዊ የመኪና መንገዶች

የዓለም የሙቀት መጠን መጨመር በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ ያሉ ከተሞች ...