ሳፋሪኮም ከፔይፓል ጋር በመሆን ኤምፔሳን በፔይፓል አለም አቀፍ የክፍያ ስርዓት ውስጥ ለማካተት አጋር ሲሆን በአጋርነቱ መሰረት 35 ሚሊየን የኤምፔሳ ደንበኞች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።
በአጋርነቱ መሰረትም ተጠቃሚዎች የፔይፓል አካውንታቸውን ከኤም ፔሳ ጋር በማስተሳሰር የገንዘብ ዝውውሮችን በቀላሉ ማከናወን ይችላሉ ተብሏል።
ለጊዜው አገልግሎቱ በኬንያ በሚገኙ ተጠቃሚዎች ላይ የሚጀመር ሲሆን በሂደት ኤም ፔሳ ወደሚሰራበቸው ሌሎች አካባቢዎች ይስፋፋል ተብሏል።
ሳፋሪኮም በኤምፔሳ ሱፐር አፑ ሰዎች በቀጥታ ከፔይፓል ገንዘብ ማውጣት እንዲችሉ የሚያስችል አማራጭንም አካቷል።
ሰዎች በቀጥታ የፔይፓል ገንዘባቸውን ከኤምፔሳ ማውጣታቸው በተለያየ መንገድ የሰሩትን ገንዘብ ሳይንዛዛ በቀጥታ እንዲያወጡ ያስችላል።
በተጨማሪ ተጠቃሚዎች ሁለቱን አካውንቶች በማስተሳሰር በቀላሉ የገንዘብ ዝውውሮችን መፈፀም ይችላሉ ተብሏል።
ኤም ፔሳ በአፍሪካ ቀዳሚው የሞባይል ገንዘብ መተግበሪያ እንደሆነ ሲዘገብ ከ50 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን በማፍራት በየዕለቱ ከ1.1 ቢሊየን ዶላር በላይ የገንዘብ ዝውውሮችንም ያሳልጣል።
ፔይፓል በአለም አቀፍ ደረጃ ከ400 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎች ሲኖሩት በተለይ ለኦንላይን ስራዎች ዋነኛ የክፍያ አማራጭ ሆኗል።
በኬንያ በሚገኘው ኤምፔሳ የሚጀምረው አገልግሎት ወደ ኢትዮጵያም እንደሚመጣ ሲጠበቅ በርካታ ወጣቶች በኦንላይን ስራዎች ያገኙትን ገንዘብ በቀላሉ እንዲያወጡ ያስችላል።
Source: tikvahethmagazine
