ስለ ሕግ

Date:

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት በአንቀጽ 105 ላይ የሕገመንግሥት መሻሻል አስመልክቶ ተከታዩን ይላል፡፡

አንቀጽ 105 ሕገ መንግሥቱን ስለማሻሻል

1 በዚህ ሕገ መንግሥት ምዕራፍ ሦስት የተዘረዘሩት መብቶችና ነጻነቶች በሙሉ፣ይህ አንቀጽ፣ እንዲሁም አንቀጽ 104 ሊሻሻሉ የሚችሉት በሚከተለው አኳቃን ብቻ ይሆናል፡፡

ሀ/ ሁሉም የክልል ምክር ቤቶች የቀረበውን ማሻሻያ በድምጽ ብልጫ ሲያጸድቁት፣

ለ/ የፌዴራሉ መንግሥት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምጽ የቀረበውን ማሻሻያ ሲያጸድቀው፣ እና

ሐ/ የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምጽ ማሻሻያውን ሲያጸድቀው ነው፡፡

2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ከተዘረዘሩት ውጭ ያሉት የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች ሊሻሻሉ የሚችሉት በሚከተለው አኳኊን ብቻ ይሆናል፤

ሀ/ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በጋራ ስብሰባ በሁለት ሦስተኛ ድምጽ የቀረበውን ማሻሻያ ሲያጸድቁት፣ እና ለ/ ከፌዴሬሽኑ አባል ክልሎቸ ምክር ቤቶች ውስጥ የሁለት ሦስተኛ ክልሎች ምክር ቤቶች በድምጽ ብልጫ የቀረበውን ማሻሻያ ሲያጸድቁት ነው፡፡

ጠቅላላ ዕውቀት

የኢትዮጵያ 81ዱ ብሔር ብሔረሰቦች ስም ዝርዝር ፡-

1. ኦሮሞ

2. አማራ

3. ሶማሌ

4. ትግራይ

5. አፋር

6. ሲዳማ

7. አገው

8. ዎላይታ

9. ከምባታ

10. ሀዲያ

11. ጋሞ

12. ጉራጌ

13. ኢሮብ

14. አርጎባ

15. ስልጤ

16. ሺናሻ

17. አኝዋክ

18. ኑዌር

29. ሀመር

20. ኩናማ

21. ጉምዝ

22. በርታ

23. በና

24. አሪ

25. ሙርሲ

26. ቡሜ

27. ካሮ

28. ፀማይ

29. ኮንሶ

30. ዳሰነች

31. አላባ

32. አርቦሬ

33. ባጫ

33. ቤንች

35. ባስኬቶ

36. ቡርጂ

37. ጫራ

38. ጋዋዳ

39. ጌዲኦ

40. ጊዶሌ

41. ጎፋ

42. አደሬ

43. ከፊቾ

44. ኮንታ

45. ኒያንጋቶም

46. ናኦ

47. ቀቤና

48. ሱርማ

49. ጠንባሮ

50. የም

51. ዲዚ

52. ዶንጋ

53. ዳውሮ

54. ዲሜ

55. ምዓን

56. ኮሞ

57. ማረቆ

58. ሞስዬ

59. ኦይዳ

60. ቦዲ

61. ፈዳሼ

62. ኮሬ

63. ማሌ

64. ማኦ

65. መሰንጎ

66. መዠንገር

67. ቀዋማ

68. ቀጨም

69. ሸኮ

70. ዘየሴ

71. ዘልማም

72. ሽታ

73. ቤተ እስራኤል

74. ማሾላ

75. ኮጉ

76. ድራሼ

77. ገባቶ

78. ጌዲቾ

794. ብራይሌ

80. ሙርሌ

81.ኮንቶማ…. ናቸው።

የኢትዮጵያ ታሪክ ከሚል የተወሰደ።

ድንቃይ

የሰሜን ኮሪያው መሪ የሴት ልጄን ስም ማንም ሊጋራት አይችልም ማለታቸው ተነገረ፡፡ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የሴት ልጅ ስምን ሌሎች ሴቶች መጠቀም አይችሉም መባሉ ተገልጿል። የአሜሪካው ራዲዮ ፍሪ ኤዥያ ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳስነበበው፥ የኪም ጆንግ ኡን ልጅ ስም (“ጁ ኤ”) የሚጠሩ ሴቶች ስማቸውን በአፋጣኝ እንዲቀይሩ ታዘዋል። ፒዮንግያንግ የፍቅር ስሞች “ቦምቡ፣ ሽጉጤ” እና መሰል ወታደራዊ ስሜት ባላቸው ስሞች እንዲቀየሩ ማዘዟም ይታወሳል ።

ከእንስሣት ዓለም

አዋልዲጌሳ

  • የአዋልዲጌሳ ጥርሶች ለየት ያሉ ናቸው። የፊት ጥርስ እና የውሻ ክራንቻ የላቸውም ነገር ግን 20 መንጋጋ ጥርሶች አሏቸው፤
  • ጠርሶቻቸው ውስጥ ብዙ ትቦዎች አሏቸው፤
  • በየ ጣቶቻቸው ጫፍ ላይ አካፋ የመሳሰሉ ረጃጅም ጠንካራ ኮኮኔዎች አሏቸው። ይሄም ጉድጓድ በፍጥነት ለመቆፈር ይረዳቸዋል፤
  • አዋልዲጌሳ ከአጥቢዎች ሁሉ የበለጠ የመቆፈር ችሎታ አላቸው፤
  • ክብደታቸው እስከ 65 ኪ.ግ ይደርሳል፤
  • አዋልዲጌሳዎች በአብዛኛው ጊዜ የሚንቀሳቀሱት በ ለሊት ነው፤
  • በበጋ የሚመገቡት ጉንዳን ሲሆን በ ክረምት ደግሞ ምስጥ ይመገባሉ፤
  • አዋልዲጌሳዎች ጉድጓዳቸውን ለቀው ሲወጡ ሌሎች እንደ ከርከሮ እና እንደ እባብ አይነት እንስሳቶች ገብተው ይኖሩበታል፤
  • ልክ እንደ ድመት አዋልዲጌሳዎች ዓይነ ምድራቸውን ጉድጓድ ቆፍረው ከተፀዳዱ በኋላ በጥንቃቄ ይቀብራሉ፤
  • ከ 7 እስከ 8 ወራቶች አርግዘው አንድ ግልገል ይወልዳሉ፤

ምንጭ :- አጥቢዎች መጽሐፍ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የህወሓት የቃላት ጦርነት ንሯል።ይዋጉ ይሆን?

ሶስቱም ኃይላት የጦር ኃይላቸዉን እያጠናከሩ፣ አዳዲስ ተዋጊ እየመለመሉ መሆናቸዉ...

የሐማስ ታጣቂዎች ከእስራኤል ጋር በመተባበር የተከሰሱ ሰባት ሰዎችን ገደሉ

ሰኞ እለት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ ያለ ቪዲዮ እንደሚያሳየው...