በማህበራዊ ሚዲያ ስለሚፈጸሙ ወንጀሎች

Date:

በማህበራዊ ሚዲያ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በመከታተል ተጠያቂነትን ለማስፈን የፎረንሲክ ቴክኖሎጂ አቅምን የማሳደግ ስራ በስፋት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ ያስጠናውን ጥናት ይፋ ባደረገበት ወቅት እንደተገለጸው፤ ተጠርጣሪዎች የሐሰት መታወቂያ እና የተጭበረበሩ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን በመጠቀም ወንጀል ፈጽመው ለመሰወር የሚያደርጉት ጥረት ለፖሊስ ምርመራ ትልቅ ፈተና ሆኖ ቆይቷል። አሁን ላይ እነዚህን ክፍተቶች የሚሞሉ የቴክኖሎጂ አሰራሮች እየተዘረጉ እንደሚገኙም ተመላክቷል።

በተለይም የብሄራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ምዝገባ ወንጀሎችን ለመቀነስና ተጠርጣሪዎችን በፍጥነት ለይቶ ለህግ ለማቅረብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተጠቅሷል።

ከዚህ ቀደም በማህበራዊ ሚዲያ የቪዲዮና የጽሁፍ ማጭበርበር ሰርተው በባንክ ገንዘብ የሚቀበሉ ወይም ህገ-ወጥ የመድሃኒት ማስታወቂያዎችን በማሰራጨት ህዝብን ለአደጋ የሚያጋልጡ ግለሰቦችን አድራሻ ማግኘት ፈታኝ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፤ አሁን ግን ባንኮችና ተቋማት ከዲጂታል መታወቂያና አሻራ ጋር መተሳሰራቸው ወንጀለኞችን ተጠያቂ የማድረግ ሂደቱን እያቀለለው ይገኛል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ሹመት

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ሌ/ጄኔራል በላይ...

የብፁዕ አቡነ ሉቃስ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ

  የሥርዓተ ቀብር መረጃ:- የሰቲት ሁመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት...

የዛሬ ዘጠኝ ጨዋታዎች

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ3ኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት...

በ20 ሚሊዮን ብር የተገዛ የእንስሳት መድኃኒት የጥራት ችግር ነበረበት

በግዢ ሂደት ውስጥ በተደረጉ ማሻሻያዎችና የላቦራቶሪ ማረጋገጫዎች የከፋ የጥራት...