በሩሲያ የፑቲን “የአገዛዝ ለውጥ” መደረግ አለበት!

Date:


‎
‎የዩኤስ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ የዩክሬንና ሩሲያ የሰላም ስምምነት ለማምጣት ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር መወያየታቸው ተሰማ ።
‎
‎የዩኤስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ክሬምሊን በዩክሬን ላይ የሚካሄደውን ጦርነት እንዲያቆም ወይም አዲስ ዙር ማዕቀብ ሊጣልበት የቀረው የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ ሁለት ቀናት ሲቀሩት የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ሞስኮ መገኘታቸውንና ከፑቲን ጋር ተገናኝተው መወያየታቸዉን ሞስኮ ታይምስ ዘግቧል ።
‎
‎ለሦስት ሰዓታት ያህል ከቆየው ስብሰባ በኋላ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ ውይይቱን “ጠቃሚ” እና “ገንቢ” ሲሉ ገልጸውታል።
‎
‎በዩኤስ የቀድሞ አምባሳደር ኡሻኮቭ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት “የዩክሬንን ጉዳይ በተመለከተ የተወሰኑ መልካም የሰላም ምልክቶችን ታይተዋል፣ እናም ሩሲያ ያቀረበቻቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ከፕሬዚዳንት ትራምፕም ተቀብለዋል። ብለዋል ።
‎
‎በመካከለኛው ምስራቅ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው የሚያገለግሉት ዊትኮፍ ትራምፕ በጥር ወር ስልጣን ከያዙ በኋላ ወደ ሩሲያ ብዙ ጊዜ ተጉዘዋል። ልዑኩ ለመጨረሻ ጊዜ ሀገሪቱን የጎበኙት በሚያዝያ ወር ሲሆን ከፑቲን ጋር በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል የሚደረገውን ቀጥተኛ የሰላም ድርድር ማደስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተው ነበር ።
‎
‎ወደ ሩሲያ ያደረጉት የቅርብ ጊዜ ጉዞ የመጣው ትራምፕ ቀጣይነት ያለው ጦርነት እንዲያቆም ወይም አዲስ ማዕቀብ እንዲጣልባት እስከ አርብ ለሞስኮ ቀነ ገደብ ከሰጡና ቻይና እና ህንድን ጨምሮ ቁልፍ የንግድ አጋሮቿን ያነጣጠረ “ሁለተኛ ታሪፍ” በማለት የጠሩን ማዕቀብ እንደሚጥሉ ካስፈራሩ በኋላ ነዉ ።
‎
‎በአሜሪካ በኩል የቀረበው ቅድመ ሁኔታሞስኮ የኔ ነው ከሚላቸው አራት የዩክሬን የምስራቅ ክልሎች የዩክሬን ሃይሎች ሙሉ በሙሉ መውጣታቸውን እንዲሁም ኪየቭ ገለልተኛ አቋም መቀበል እና በወታደራዊ ኃይሏ መጠን ላይ ገደብ መቀበልን ያካትታል ተብሏል።
‎
‎ኪይቭ በበኩላቸው አፋጣኝ የተኩስ ማቆም ጥሪ እያቀረቡ ሲሆን ባለፈው ሳምንት አጋሮች በሞስኮ ውስጥ “የአገዛዙ ለውጥ” እንዲመጣ ጥሪ አቅርበዋል ። የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ረቡዕ ማለዳ ላይ እንዳሉት “ሞስኮ የአለምን ጫና ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ጫና ፣ ጦርነቱን ለመቀጠል የጠንካራ ማዕቀብ ስጋት መሰማቷ በጣም አስፈላጊ ነው” ብለዋል ።
‎
‎ ምንጮች ለብሉምበርግ እንደተናገሩት የሩሲያ ኃይሎች በጦር ሜዳው ላይ የማያቋርጥ ግስጋሴ እያደረጉ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ክሬምሊን ወታደራዊ ዘመቻውን ለማስቀጠል ትራምፕን ለማረጋጋት ከዩክሬን ጋር የአየር ላይ የተኩስ አቁም እድልን እያጤነ ነው ። ሆኖም ፑቲን ሰፋ ያለ የተኩስ አቁም ስምምነትን ለጊዜው ለመስማማት አላሰቡም ሲል ዘግቧል።
‎
‎ለዘገባው ሞስኮ ታይምስ ብሉምበርግ አልጀዚራን ተጠቅመናል ።
‎
‎የኔታ ቲዩብ
‎

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከጥር 1 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ለጫት ላኪዎች የቅድመ ፈቃድ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መስጠት ይቆማል

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከጫት ወጪ ንግድ ፈቃድና የብቃት...

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ሪፖርትን እስከ ነገ በቅጣት እንደሚቀበል አስታወቀ

  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር...

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...