በአዲስ አበባ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት፣ ዲፕሎማቶች፣ የአፍሪካ ህብረት ሠራተኞችና የከተማዋ ነዋሪዎች በጋራ የተሳተፉበት የ5 ኪ.ሜ ሩጫ ተካሄደ።
ዝግጅቱ የአፍሪካዊ አንድነትን፣ የወንድማማችነትና እህትማማችነት መንፈስን እንዲሁም አዲስ አበባ የሰላምና የዲፕሎማሲ ማዕከል መሆኗን የሚያጎላ መሆኑ ተገልጿል።
አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና እንደመሆኗ፣ የአህጉሪቱን ሕዝቦች የሚያቀራርቡና የጋራ አንድነትን የሚያጠናክሩ እንዲህ ያሉ ዝግጅቶች በተጠናከረ ሁኔታ እየተካሄዱ መሆኑ ተጠቁሟል።
በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉት የኮሪደር ልማትና የከተማ ማስዋብ ሥራዎች ለነዋሪዎችና ለዲፕሎማቶች ምቹ፣ ጽዱና ለጤናማ አኗኗር ተስማሚ ከተማ ለመፍጠር ያላቸውን አስተዋጽኦ በዝግጅቱ ላይ ማሳየቱን ተዘግቧል።
