ጤና ሚኒስቴር ከለሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወርን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የእግር ጉዞ መርሃግብር አካሂዷል።
በመርሃግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት በጤና ሚኒስቴር ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እና የአዕምሮ ጤና ዴስክ ሀላፊ ሰላማዊት አየለ (ዶ/ር)፣የጡት ካንሰር በኢትዮጵያ የመጀመርያው እና በገዳይነቱ የሚታወቅ የካንሰር አይነት ነው ያሉ ሲሆን፣ በኢትዮጵያም በዓመት ውስጥ ብቻ ከ18ሺህ በላይ ሴቶች በጡት ካንሰር በሽታ ይጠቃሉ ብለዋል።
ጤና ሚናስቴርም አስቀድሞ መመርመርን መርህ በማድረግ አክሞ እሰከ ማዳን ድረስ እስትራቴጂ ነድፎ እየሰራ እንደሚገኝ
