በክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማሰብ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ዓለም አቀፍ ዘመቻ እያካሄዱ ነው።

Date:

በመላው ዓለም በእምነታቸው ምክንያት ስደትና መከራ የሚደርስባቸውን ክርስቲያኖች ለማሰብ የሚካሄደው ዓመታዊው የ”ቀይ ሳምንት” ዘመቻ በፓሪስ ከሚገኘው የኖትር ዳም ካቴድራል ጀምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ከኅዳር 6 እስከ 13 በሚቆየው በዚህ ዘመቻ  130 ታዋቂ ካቴድራሎች እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ አብያተ ክርስቲያናት፣ ሐውልቶች እና የሕዝብ ሕንፃዎች በቀይ ብርሃን ይታያሉ።

እንደ አዘጋጆቹ ገለጻ ቀዩ ብርሃን ስለ ክርስቶስ ሲሉ ሕይወታቸውን የሰጡ ሰማዕታትን ደም የሚወክል ሲሆን በሳምንቱ ውስጥም በተለያዩ ስፍራዎች የጸሎት ሥነ-ሥርዓቶች እና ሕዝባዊ ስብሰባዎች ለማካሄድ በዓለም ዙሪያ ከመቶ ሺዎች በላይ የሚሆኑ ሰዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ዘመቻውን ከተቀላቀሉት የፈረንሳይ ዋና ከተማ አንዱ የሆነው የኖትር ዳም ካቴድራል ባወጣው መግለጫ፣ መርሐ-ግብሩ በስደት እና በመከራ  ላይ ባሉ ክርስቲያኖች ዙሪያ ያለውን ዝምታ ለመስበር እና ዓለም እንዳልረሳቸው ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን አሳውቋል።

መረጃው የ Christian devotion  ነው

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ነገ በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመጪው ሐሙስ ህዳር 17...

ከፍተኛ የወጪ ንግድ ገቢ ያስመዘገቡ ድርጅቶች ተሸለሙ

በጥራጥሬና ቅባት እህሎች ዘርፍ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ገቢ ያስገኙ...

ዓለም አቀፉ ሽልማት ለጋዜጠኛ ይስሐቅ በላይ ተሰጠዉ

ዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ (IOC) በ4ኛው የዓለም የወጣቶች ኦሎምፒክ...

የተመድ ዋና ፀሐፊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስጋቶችን ለመቆጣጠር ዓለም አቀፍ ትብብር ጠየቁ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ፣ የሰው ሰራሽ...