“ባለፉት 8 ዓመታት እንደ ላሚን ያማል ዓይነት ድንቅ ተጫዋች አይቼ አላውቅም” – ሲሞን ኢንዛ

Date:

“ባለፉት 8 ወይም 9 ዓመታት እንደ ላሚን ያማል ዓይነት ድንቅ ተጫዋች አይቼ አላውቅም” ሲሉ የኢንተር ሚላን አሠልጣኝ ሲሞን ኢንዛጊ ለተጫዋቹ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ዛሬ ምሽት በተደረገው የሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታ ባርሴሎና ኢንተር ሚላንን በሜዳው አስተናግዶ 3 አቻ ተለያይቷል።

በጨዋታው የባርሴሎናው አዳጊ ተጫዋች ላሚን ያማል ድንቅ ብቃቱን ያሳየ ሲሆን ጠንካራ የሚባለውን የኢንተር ሚላን የተከላካይ መስመር አታልሎ በማለፍ ለክለቡ አንድ ግብ አስቆጥሯል።

የ17 ዓመቱ ላሚን ያማል በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ታሪክ በግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ግብ ያስቆጠረ በዕድሜ ትንሹ ተጨዋች ሆኗል።

በዚህ ብቃቱ የተደነቁት የኢንተር ሚላኑ አሠልጠኛል ሲሞን ኢንዛጊ፣ “የእሱን እንቅስቃሴ ለመግባት ሁለት እና ሦስት ተጫዋችን መመደብ ነበብን” ሲሉ ከጨዋታው በኋላ ተናግረዋል።

“እንደ ላሚን ያማል ያሉ ባለድንቅ ተሰጥኦ ተጫዋቾች በየ50 ዓመቱ አንዴ የሚከሰቱ ናቸው” ሲሉም ነው አድናቆታቸውን የገለጹት።

የባርሴሎናው የአጥቂ መስመር ተጫዋች ላሚን ያማል በ17 ዓመቱ ዛሬ 100ኛ ጨዋታውን ማድረግ ችሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

BYD ከ115,000 በላይ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ላይ ማሻሻያ እንደሚያስፈልጋቸው ገለጸ

የቻይናው ግዙፉ የኤሌትሪክ መኪኖች አምራች ቢ.ዋይ.ዲ በዲዛይንና በባትሪ ተከላ...

የትራምፕን ንግግር የህንድ መንግስት ስለ ጉዳዩ ምንም የማዉቀዉ ነገር የለም ብሏል

የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የሩሲያን ነዳጅ ላለመግዛት መስማማታቸውን...

አቶ አህመድ ሽዴ ከእንግሊዝ የዓለም አቀፉ የልማት እና የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከእንግሊዝ የአለም አቀፍ የልማት...