የብሪታኒያ መከላከያ ሚኒስቴር ለባህር ኃይል እና ለአየር ኃይል ሠራዊቱ እገዛ የሚያደርግ አዲስ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን ሥራ ላይ ሊያውል ነው።
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ ይህንኑ እውን ማድረግ የሚያስችል ልምምድ በምድር፣ በውኃ እና በአየር በተሳካ መልኩ ማድረጉን ገልጿል።
ይህ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ሀገሪቱን በውስጥ ደኅንነቷ የተጠበቀ እና በውጭ ደግሞ ጠንካራ ለማድረግ ጥቅም ላይ ይውላል ተብሏል።
የብሪታኒያ የመከላከያ ሚኒስቴር እንደገለጸው፣ በጦር ሜዳ ላይ እነዚህን የሰው ሠራሽ አስተውሎት መሣሪያዎች መጠቀም የሥራ ጫናን ይቀንሳል።
ከዚህ ቀደም አንድ አብራሪ አውሮፕላኑን ማብረር፣ ከአደጋ መጠበቅ እና የመገናኛ መሣሪያዎችን በተመሳሳይ ጊዜ መጠቀም ይኖርበታል።
እነዚህን የሰው ሠራሽ አስተውሎት መሣሪያዎች ደግሞ ከሥራዎቹ ውስጥ አንዳንዶቹን በመሥራት አብራሪው በተሻለ ሁኔታ አንድ ነገር ላይ እንዲያተኩር ይረዱታል።
የሰው ሠራሽ አስተውሎቱ ከሚሠራው ሥራም አንዱ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን መቆጣጠር እና መምራት ነው።
እንዲሁም ለፓይለቱ (አብራሪው) ጥቆማዎችን መስጠት፣ ደኅንነታቸው የተጠበቀ መንገዶችን ማሳየት፣ እና በአደገኛ ተልዕኮዎች ወቅት አንዳንድ መቆጣጠሪያዎችን ሊቆጣጠር ይችላል ሲል የዘገበው ዘ ቴሌግራፍ ነው።
