ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን ሳር ቅጠሉ የሚወዳቸው

Date:

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን ሳር ቅጠሉ የሚወዳቸው የሀይማኖት አባት ስለሆኑ አይደለም። ‘ሰው’ ሆነው ስለተገኙ እንጂ።

  • አላህን እንደሚፈሩ ያያቸው ሁሉ መገንዘብ አያቅተውም።
  • ከእውነት ጎን ለመቆም ማንንም አይፈሩም፤ አያስፈቅዱምም።
  • ሙስሊም ክርስትያን ሳይሉ ከተበደለ ጎን ይቆማሉ።
  • ንግግራቸው ብቻ ያጠግባል፤ ነፍስን ያለመልማል።
  • አመራር (leadership) ያውቃሉ። ፕሮሲጀር እንዴት እንደሚጠብቁ አብሯቸው የሰራ ይመስክር።
  • ዑለማዎችን (አዋቂዎችን) ያከብራሉ።
  • በኢትዮጵያ ጉዳይ ቀልድ አያውቁም። (በአባይ ውሃ አጠቃቀም ዙሪያ በልበ-ሙሉነት ያንፀባረቁት አቋም የግብጽ መሪዎችን እንዴት እንዳነጋገረ እናስታውሳለን)።
  • በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰነድ-አልባ የሙስሊሙ መገልገያ ተቋማት (መስጊዶችን ጨምሮ) ይዞታዎች በጥሩ ተግባቦት ህጋዊ መስመር አስይዘዋል።

ሌላም ሌላም ብዙ…. መልካም ነገሮች …

አላህ (ሱ.ወ) የተቀዳሚ ሙፍቲያችንን አፊያ ይመልስልን! 🤲
ሁላችንም በየእምነታችን ዱዓ (ጸሎት) በማድረግ ፈጣሪ ጤናቸውን እንዲመልስላቸው እንለምን! 🤲
ሐዉልት አህመድ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ለሊት እንቅልፍ የለኝም

"አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ያሳስበኛል፤ እኔ አሁን 86 ዓመት...

አዎ ነበሩ ….

🔘የሁሉም አባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሓጅ ዑመር🔘ነፍስዎ በሰላም ትረፍ "...

ሕይወታቸው የሚያጓጓ ፣ እረፍታቸው የሚያስቀና

          ተቀዳሚ ሐጂ ሙፍቲ ዑመር ኢድሪስ በማረፍ ከፍተኛ ሀዘን...