“አሁን መልሶ ግንባታ እንጀምራለን”- ዶናልድ ትራምፕ

Date:

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስራኤል ምክር ቤት ንግግር ካደረጉ በኋላ ወደ ግብፅ አቅንተዋል።

በግብፅ፣ ሻርም ኤል-ሻይክ ከ20 በላይ የሚሆኑ የአገራት መሪዎች ተሰባስበው በቀጣዩ የጋዛ የሰላም ዕቅድ ላይ ተወያይተዋል።

ግብፅ፣ ኳታር፣ ቱርክ እና አሜሪካ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ጠባቂዎች ሆነው ፊርማቸውን አኑረዋል።

“አዲስ ውብ ቀን መጥቶልናል። አሁን ጊዜው መልሶ የመገንባት ነው” ብለዋል ትራምፕ።”ለመካከለኛው ምሥራቅ ታሪካዊ ቀን ነው” ሲሉም አክለዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስራኤል ምክር ቤት ንግግር ካደረጉ በኋላ ወደ ግብፅ አቅንተዋል።

በግብፅ፣ ሻርም ኤል-ሻይክ ከ20 በላይ የሚሆኑ የአገራት መሪዎች ተሰባስበው በቀጣዩ የጋዛ የሰላም ዕቅድ ላይ ተወያይተዋል።

ግብፅ፣ ኳታር፣ ቱርክ እና አሜሪካ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ጠባቂዎች ሆነው ፊርማቸውን አኑረዋል።
“አዲስ ውብ ቀን መጥቶልናል። አሁን ጊዜው መልሶ የመገንባት ነው” ብለዋል ትራምፕ።

“ለመካከለኛው ምሥራቅ ታሪካዊ ቀን ነው” ሲሉም አክለዋል።

ትራምፕ የሰላም ዕቅዱ ሁለተኛ ክፍል ተጀምሯል ብለዋል።

ትራምፕ በግብፁ ውይይት ላይ “ሁሉም ሰው ደስተኛ ነው። እዚህ ለመድረስ 3,000 ዓመታት መውሰዱን ታምናላችሁ? ብለዋል።

የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደልፋታሕ አል-ሲሲ በአገራቸው ትልቁ የሆነውን ‘ኦርደር ኦፍ ዘ ናይል’ ሽልማት ለትራምፕ ሰጥተዋል።
አል-ሲሲ “አስከፊው ጊዜ ያከተመበት ታሪካዊ እርምጃ ነው” ሲሉ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የህወሓት የቃላት ጦርነት ንሯል።ይዋጉ ይሆን?

ሶስቱም ኃይላት የጦር ኃይላቸዉን እያጠናከሩ፣ አዳዲስ ተዋጊ እየመለመሉ መሆናቸዉ...

የሐማስ ታጣቂዎች ከእስራኤል ጋር በመተባበር የተከሰሱ ሰባት ሰዎችን ገደሉ

ሰኞ እለት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ ያለ ቪዲዮ እንደሚያሳየው...