የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር ሻብያን ነክሰው ይዘዋል፡፡ ዛሬ ደግሞ፣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እንደ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም ፈርጥጠው ከአገር ይወጣሉ ይህም በቅርብ ይሆናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
የአሰቡ ዘመቻ ከተጀመረ ኢሳያስ ከስልጣን ይወገዳሉ የሚል ትንተና እየተሰጠ ባለበት በዚህን ወቅት አምባሳደሩ ያሰሙት ጉዳይ ሻብያን ያስደነገጠ እና ያሸበረ ሆኗል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከጸረ ሻብያ ቡድኖች ጋር አምባሳደሩ በአሜሪካ እንደመከሩም ታውቋል፡፡
የቀድሞው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ቲቦር ናጂ የአስመራውን መንግስት በተመለከተ አነጋጋሪ አስተያየቶችን መስጠት ቀጥለዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም ከጸረ ሸብያ ከሆኑ ድርጅቶች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ እያሳደጉ ይገኛል፡፡
አምባሳደሩ በትናንትናው እለትም ከብርጌድ ንሓምዱ የሰማያዊ ማዕበል ንቅናቄ መሪዎች ጋር በአሜሪካ መወያየታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ ከሰማያዊ ማእበል ንቅናቄ መሪዎች ጋር መወያየታቸውን በገለጹበት የኤክስ ልጥፋቸው ላይ፣ ‹‹ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከዚህ ቀደም እንደነበሩ አምባገነኖች ሁሉ ከአገር ይኮበልላሉ›› ብለዋል፡፡
አምባሳደሩ ከዚህ ቀደም በአለም ላይ ያለፉ እንደ መንግስቱ ኃይለማሪያም እናጋዳፊ ያሉ አምባገነን መሪዎችን በመጥቀስ የኢሳያስ አፈወርቂም እጣ ከዚህ የሚለይ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮ ኤርትራ መሀል ውጥረቱ እጅግ መባባሱን ተከትሎ ውጊያ የሚነሳ ከሆነ ጦርነቱ ሁለት ውጤት ሊነኖረው እንደሚችል ተንታኞች በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡፡ አንደኛው ኢትዮጵያ አሰብን የመቆጣጠሯ ነገር ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከስልጣን የመወገድ ጉዳይ ነው፡፡
ከወራቶች በፊት የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አዛዥ የነበሩት ጀነራል አበበ ተክለሀይማኖት በሰጡት አንድ አስተያት፣ ጦርነቱ የሚነሳ ከሆነ በርግጥም የሻብያ ግብአተ መሬት የሚፈጸምበት ሊሆን ይችላል ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠው ነበር፡፡
ዛሬ ደግሞ አምባሳደር ቲቦር ናጂ የቀድሞው አምባገነን መሪዎችን በመጥቀስ የኢሳያስ እጣ ፈንታም ከዚህ የሚለይ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡
andafta