“የጽናት ናሙና” መጽሐፍ ተመረቀ

Date:

በሀገረ አሜሪካ ከሁለት ዐሥርተ ዓመታት በላይ የኖሩት ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቶ ኤርሚያስ መኮንን” የጽናት ናሙና” በሚል ርዕስ የከተቡት ጥበባዊ ሥራ፣ ጥቅምት 6 2018 ዓ.ም በሒልተን ሆቴል በደማቅ ሥነሥርዓት ተመረቋል።

በምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ዳይሬክተር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ፤የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሸነር ዶ/ር ዮናሰ አዳዬ፤ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ጀግኖች ማኅበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ደራሲ፣ ሕዳሴው ግድብ ከጥንስሱ ጀምሮ እሰከ መቋጫው ባለፈባቸው ፈታኝ ዓመታት ውስጥ የድርሻቸውን ሲወጡ ቆይተዋል፡፡በተለይም፤ በውጪ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን በማነሳሳት፣ በርካታ የቦንድ ሽያጭ እንዲካሄድ፣ ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል።

ከዚኽም በተጨማሪ፣ በአፍሪቃ ሀገራት በመዘዋወር፣ የኢምባሲ እና ቆንስላ ጽ/ቤት ተወካዮችን በማስተባበር “የፐብሊክ ዲፕሎማሲ” ሥራ ሠርተዋል፡፡ ይኽም አበርክቷቸው ከግምት ተጥፎ፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸኋል፡፡

አቶ ኤርሚያስ፣በሀገር ፍቅር ስሜት ሲቃትቱለት የነበረው አባይ ወንዝ፣በከንቱ የሚፈስበት ዘመን አክትሞ ለፍሬ ሲበቃ በመመልከታቸው፣ ራሳቸውን “ሕልሙ እንደተሳካለት ዕድለኛ ደራሲ” ነው፤የሚቆጥሩት፡፡

ደራሲው የሕዳሴው ግድብ የመሠረት ድንጋይ ከመቀመጡ ከስድሰት ዓመት በፊት፣በአባይ ወንዝ ዙሪያ የተፈጠረባቸውን ሀገራዊ ቁጭት ተንተርሰው ያሰናዱት ይህ መጽሐፍ ፣ በ14 ምዕራፎች ተከፍሎ በ197 ገጾች የተቀነበበው ሲሆን፤ በ1000 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...