የሥነጥበብ ባለሙያዎቻችን በዓለም አቀፍ መድረክ ስራዎቻቸውን እያሳዩና ሐገራቸውንን እያስተዋወቁ ይገኛሉ::
ሠዓሊ እያዩ ገነት በጣልያ በ10ኛው አለምአቀፍ የስነጥበብ መድረክ ኢትዮጵያንና አፍሪካን በመወከል ተሳትፎ ሀገሩን አስተዋወቀ ይገኛል:: ።
ሠዓሊ እያዩ ገነት በጣልያ 10ኛው አለምአቀፍ የስነጥበብ መድረክ ላይ ስላከናወነው ተግባር ገብረማርያም ይርጋ ይህንን ፁሑፍ በገፁ ላይ አጋርቶናል::
በባህርዳር መቀመጫውን ያደረገ እና በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሰዓሊና መምህር የሆነው የእይታ ጥበብ ባለሙያ ኤ ሴ ሰታንቴ (a Se Stante Associazione sociale APS )በተባለ ተቋም ተዘጋጅቶ በቀረበ በጣሊያን በሚገኝ 10ኛው አለምአቀፍ የስነጥበብ ቢናሌ በሳንታ ማሪያ ዲ ሳላ ፣ቬንስ (Art biennial ) ሰአሊ እና መምህር አርቲስት እያዩ ገነት ተሳትፏል ።
ይህ አውደርእይ የሚላን ፣ቬንስ እና ታላላቅ ከንቲቫዎች የባህል አታሼዎች በተገኙበት በOctober 5 ,2025 ተከፍቷል ።
ይህም ከ68 በላይ ሰዓሊያን የተለያየ ሀገራትን የወከሉ ሲሆን በዚህ ዙር ደግሞ እያዩ ገነት ኢትዮጵያንና አፍሪካን በመወከል ተሳትፏል ።
በዚህም የሀገር ባንዲራ በታላቁ ቪላ ዴል ፋሪሴቲ እንዲሰቀል ሆኗል። አውደርእዩ እንደ እኤአ ከOctober 5,2025-26,2025 ለህዝብ እይታ ክፍት ሆኗል ።
በዚኹ መድረክ የኢትዮጵያን ጥበብና እሴቶች የማስተዋወቅ ስራ ሰርቷል ። አርቲስቱ ኢጣሊያ ሲደርስ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን ከተለያዩ ሀገራት ከመጡ ልዑኮች ጋር ትዉዉቅ መርሃግብር እና የክብር ግብዣ ተደርጎለታል።
አርቲስት እያዩ ገነት የስዕል ስራዎቹን በማቅረብ ሀገሩን ማስተዋወቅ፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከማድረግ ባሻገር፣ በጥበብ ዲፕሎማሲያዊ ተግባራት ኢትዮጵያዊነትን ማሳየት፣ ከተለያዩ የአለም ሃገራት ከመጡ የዘርፉ ልዑካን ጋር የልምድ ልውውጥ ማድረግ በጥበቡ ዘርፍ እንደ ሃገር ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር ጥረት አድርጓል ። እንደዚህ አይነት ባለሙያዎች ሊበረታቱ እና ሊመሰገኑ ይገባል ።
(ገብረማርያም ይርጋ )