የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ኢትዮጵያ በመርህ ደረጃ የ3.5 ቢሊዮን ዶላር የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት ከአበዳሪዎቿ ጋር እንደደረሰች አስታውቀዋል።
ሚኒስተሩ የ2017 በጀት ዓመት ሶስተኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ባደረጉት ገለጻ ከአበዳሪዎች ኮሚቴ ጋር በቅርቡ የመግባቢያ ሰነድ እንደሚፈረምና ከእያንዳንዱ አበዳሪ ሀገራት ጋር ዝርዝር ውይይቶች እንደሚደረጉ ይፋ አድርገዋል።
የዕዳ ጫናን በመቀነስ ረገድ በዚህ ዓመት ትልቅ ውጤት መገኘቱንም ሚኒስትሩ በገለጻቸው ጠቁመዋል።