ኢንቪዲያና ኦፕን ኤ.አይ የ100 ቢ. ዶላር ስምምነት አድርገዋል

Date:

በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚሰሩ ተቋማት ለቴክኖሎጂው ትግበራ የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶችን ለማምረት የሚያስችሉ ስምምነቶችን እያደረጉ መሆኑን ሮይተርስ አስነብቧል፡፡

ግዙፉ የቺፕ አምራች ኩባንያ ኢንቪዲያ እና ኦፕን ኤ.አይ የዳታ ሴንተር ቺፖችን ለማምረት የሚያስችል የ100ቢሊዮን ዶላር ስምምነት አድርገዋል፡፡

በሌላ በኩል፤ ሜታ ኩባንያን በመጪዎቹ አመታት የክላውድ ኮምፒውቲንግ ተጠቃሚ የሚያደርግ የ20 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ከኦራክል ኩባንያ ጋር ተፈርሟል፡፡

ሜታ እና ጉግል በክላውድ ኮምፒውቲንግ ላይ ለመስራት የ10 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ማሰራቸው የሚታወስ ነው፡፡ የቴስላ ኩባንያ ፈጣን የቴክኖሎጂውን ቺፖች ለመጠቀም የሚያስችለውን ስምምነት ከሳምሰንግ ጋር በ16.5 ቢሊዮን ዶላር ተፈራርሟል፡፡

በአሜሪካ የተዋወቀው እና ሶፍትባንክ፣ ኦፕን ኤ.አይ እንዲሁም ኦራክል በጋራ የሚሰሩት ስታርጌት ፕሮጀክት 500 ቢሊየን ዶላር የተመደበለት መሆኑ አይዘነጋም፡፡

በያዝነው የፈረንጆቹ አመት ተፅዕኖ ፈጣሪ የዘርፉ አንቀሳቃሽ ኩባንያዎች፣ ለቴክኖሎጂው እድገት አጋዥ የሆኑ ስምምነቶች አድርገዋል፡፡

በተለያዩ ጊዜያት የተደረጉት እነዚህ ስምምነቶች፣ በፍጥነት እያደገ የሚገኘዉን የኤ.አይ ቴክኖሎጂ አብሮ ለማልማት አስፈላጊ የሆኑ መሰረተ ልማቶችን የመገንባት ፍላጎት እያደገ ስለመሆኑ አመላካች ነው ሲል የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲዩት አስነብቧል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የህዳሴ ግድቡ ውዝግብ በፖለቲካዊ ሳይሆን በቴክኒካዊ መንገድ መፈታት አለበት

በአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ፣ እና የመካከለኛው ምስራቅ...

የ7 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ አለመከናወኑ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሚተዳደሩ 7 የጋራ መኖሪያ...

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ በ80 ዓመታቸው ከዚህ...