“እስራኤል ጦርነቱን እንድትቀጥል ላደርግ እችላለሁ” ትራምፕ

Date:


ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለእስራኤል አንዲት ቃል ባወጣ በጋዛ ያቆመችው ጦርነት ትቀጥላለች አሉ።

ትራምፕ ይህንን ያሉት እስራኤል በሀማስ የተመለሱልኝ በህይወት የሌሉ ታጋቾች እስራኤላውያን አይደሉም ማለቷን ተከትሎ ነው።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም ሀማስ የሰላም ስምምነቱን እስከ መጨረሻው የማይጓዝ ከሆነ ለጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ጦርነቱን እንዲቀጥሉ ፍቃድ እሰጣለሁ ብለዋል።

እስራኤል በበኩሏ የሀማስን ድርጊት ተከትሎ እርዳታ የሚገባበትንና ተጨማሪ ወደ ጋዛ የሚያስከቡ መስመሮችን የመክፈት እቅዷን አዘገያለሁ ብላለች።

በሌላ መረጃ ሀማስ ተጨማሪ ሁለት በህይወት የሌሉ እስራኤላውያን መመለሱን ገልፆ፤ ቀሪ በህይወት የሌሉ ታጋቾችን ለመመለስ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ገልጿል።

ቡድኑ ባወጣው መግለጫ የሰላም ስምምነቱን ለመፈፀም ቁርጠኛ ቢሆንም እስካሁን ሊደርስባቸው የቻሉ አስክሬኖችን መመለሱንና ቀሪዎቹን ለማግኘትና ለመመለስ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ተናግሯል።

ረቡዕ ምሽት የመለሳቸው ሁለት አካላት እስራኤላውያን መሆናቸው ከተረጋገጠ በሀማስ በኩል 19 በህይወት የሌሉ እስራኤላውያን ታጋቾች ቀሪ ይሆናሉ ማለት ነው።

በሰላም በስምምነቱ መሰረት ደግሞ በመጀመሪያው ምዕራፍ ሙሉ ለሙሉ ታጋቾችን መመለስን ያስገድደዋል።

ሀማስ ይህንን ለመፈፀም እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

ዘገባው የሲኤን ኤን ነው።

በ-የአብስራ ሚሊዮን

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

BYD ከ115,000 በላይ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ላይ ማሻሻያ እንደሚያስፈልጋቸው ገለጸ

የቻይናው ግዙፉ የኤሌትሪክ መኪኖች አምራች ቢ.ዋይ.ዲ በዲዛይንና በባትሪ ተከላ...

የትራምፕን ንግግር የህንድ መንግስት ስለ ጉዳዩ ምንም የማዉቀዉ ነገር የለም ብሏል

የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የሩሲያን ነዳጅ ላለመግዛት መስማማታቸውን...

አቶ አህመድ ሽዴ ከእንግሊዝ የዓለም አቀፉ የልማት እና የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከእንግሊዝ የአለም አቀፍ የልማት...