ዘንድሮ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ለዳይቨርሲቲ ቪዛ (ዲቪ) ሎተሪ ምዝገባ 1 ዶላር የአገልግሎት ክፍያ ማስከፈል ይጀምራል።
ይኸው ክፍያ ተመርጦ ወይም ዲቪ ሲደርስ ከሚከፈለው 330 ዶላር ውጪ ነው። አመልካቾች ማሸነፋቸው ሲረጋገጥ ለቪዛ አገልግሎት 330 ዶላር ይከፍላሉ።
በዚህ ወር የምዝገባው ቀን ይፋ የሚደረገው የ2027 ዲቪ ሎተሪ እንደከዚህ ቀደሙ አሰራር ከሆነ እስከ ህዳር ወር ድረስ ይቆያል (ማመለከቻ ጊዜው) ፤ ውጤቱ ደግሞ በግንቦት ወር 2026 ይታወቃል።
በየዓመቱ እንደሚደረገው 55,000 አሸናፊዎች ከመላው ዓለም ይታወቃሉ።
ለዲቪ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ስለሚያመለክቱ አሜሪካ ዘንድሮ በምትጀምረው የ1 ዶላር ክፍያ ለስራ ማስኬጃዎች የሚሆናትን በሚሊዮኖች ዶላር ታገኛለች ተብሎ ይጠበቃል።
በየዓመቱ ለአሜሪካ ዲቪ ከዓለም የተለያዩ ሀገራት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚያመለክቱ ሲሆን ለአብነት ለ2025ቱ ዲቪ ወደ 19,927,656 ሰዎች አመልክተዋል። ከነዚህም 131,060 ሰዎች ለቀጣይ ሂደት ተምርጠው ከነሱ ውስጥ 55,000 ሰዎች ቪዛው ተሳክቶላቸዋል።
@tikvahethiopia
