የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው በዚህ አመት ከሊቨርፑል የተሻለ መሆን እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል።
“ ሊቨርፑል ባለፈው አመት የሊጉ አሸናፊ ነበሩ ምክንያቱም ሻምፒዮን መሆን ይገባቸዋል “ ሲሉ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።
“ ባለፈው አመት ሊቨርፑል ምርጡ ቡድን ነበር “ ያሉት ሚኬል አርቴታ ወጥ አቋም ማሳየት እና በተለያዩ ሁኔታዎች ለማሸነፍ መንገድ ያገኘ ቡድን ነበር ብለዋል።
“ እኛም እንደ ሊቨርፑል መሆን እንፈልጋለን በዚህ አመት ከእነሱ የተሻለ መሆን እንፈልጋለን ” አርቴታ
