ከመጽሐፍት ገጾች

Date:

“ትልቁ ችሎታና መስዋዕትነት አንድን ነገር ከስር መሰረቱ ማቋቋም እንጂ ሌላው በፉበት፣ በደከመበት ወይም “ባሞቀው ቤት” በልዩ ልዩ ምክንያቶችና ቀን ቆጥሮ ተሹሞ ገብቶ ዋና መስራቾቹን መውቀስ፣ ለሰሯቸውና ላበረከቱት ስራዎች ስማቸው እንዳይነሳ አደባብሶ ባልዋለበት ሜዳ እኔን እወቁኝ ማለት ተቀባይነትን የሚያገኘው ከመሰልና ቢጤዎች ሲሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ትንሽ ወደ ኋላ መለስ ብሎ ታሪኩን ጫር ጫር ካደረገ ሰሪውንና ባለውለታውን የሚጋባ ያውቀዋል። ካለማስረጃ በነገሩኝና በነበሩ ከመነታረክ ለመዳን ማድረግም ያለብን ይኸንኑ ነው።” 

አታመንታ ጽጌ፣  ብ/ጄ ጽጌ ዲቡ

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ደቡብ ኮሪያ ልጆች ለሚወልዱ ጥንዶች 10,500 ዶላር ልትሰጥ ነው፡፡ ፍቅር ለመጀመር ለሚያስቡ ጥንዶች የፍቅር ቀጠሮ እለት የሚያወጡት ወጪ በመንግስት ይሸፈናል። በዓለም ዝቅተኛው የወሊድ መጠን ባለባት ደቡብ ኮሪያ እያሽቆለቆለ ያለው የስነ-ሕዝብ እና የኢኮኖሚ ሁኔታ አደጋ ጋርጦባታል። እ.ኤ.አ. በ2022 በደቡብ ኮሪያ ከአንዲት ሴት የሚጠበቀው አማካይ የሕፃናት ቁጥር ወደ 0.78 ዝቅ ብሏል። ይህም ካለፈው ዓመት ከነበረው 0.81 ያነሰ ሆኗል። በበለጸጉ ሀገራት ያለው በአዲስ ትውልድ መተካካት መጠን የህዝቡን የተረጋጋ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚያስፈልገው ከአንድ ጥንዶች የወሊድ ብዛት  በተለምዶ 2.1 ገደማ ቢሆን የደቡብ ኮርያ ከዚህ ያነሰ ይሆናል። ሁኔታውን ለመቀልበስ የደቡብ ኮሪያ ማዕከላዊ መንግስት እና የአካባቢ አስተዳደሮች ልጅ ለወለደ ማንኛውም ሰው ክፍያን እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን ለመስጠት እየሞከሩ ይገኛል። በአንድ ትውልድ ዘመን ተአምራታዊ በተባለ የኢኮኖሚ እድገት ከድህነት ወደ በለፀጉ ሀገራት ተርታ የተለወጠችው ደቡብ ኮሪያ በጠንካራ ማህበራዊ ደህንነትዋ ላይ ግን ስጋት ውስጥ ገብታለች። እ.ኤ.አ. ከ2022 ጀምሮ እናቶች ልጅ ሲወለዱ 2 ሚሊዮን ዎን ወይን 1,510 የአሜሪካን ዶላር የገንዘብ ክፍያ ያገኛሉ።ከዛም ልጆች ለማሳደግ ይረዳቸው ዘንድ ቤተሰቡ በወር 700,000 ዎን ወይም 528 ዶላር  በጥሬ ገንዘብ እስከ አንድ አመት ያሉ ህፃናት ወላጆች ይሰጣል። 264 ዶላር ከሁለት አመት በታች የሆኑ ህጻናት ወላጆች በየወሩ ይቀበላሉ። ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን ያካተተ ሲሆን ለነፍሰ ጡር እናቶች የህክምና ወጪዎች፣ የመካንነት ህክምና፣ የህጻናት እንክብካቤ አገልግሎት እና አዲስ ፍቅር ለመጀመር ለሚያስቡ ጥንዶች የፍቅር ቀጠሮ ቀን ወጪዎች በመንግስት ይሸፈናል።

ዳጉ ጆርናል

ሥነ-ግጥም

ነፃነት

የእገሌ ነፃ አውጪ ግንባር

የእገሌ ነፃ አውጪ ፓርቲ

እገሌ ለነፃነትና ለዴሞክራሲ…

ሁሉም ነፃ አውጪ የሚታገልባት፣

ከምን ነፃ አውጥቶ የት እንዷሚወስዳት

ያልተገለፀላት አለች ምስኪን ሀገር አውጪ የበዛባት፤

ከሁሉ የሚያስፈራው የሚያሰጋው ከቶ

ሁሉ እንጿምኞቱ እንዷህልሙ አውጥቶ

ከህዝብ ነፃ እንዳትሆን አገርነት ቀርቶ፡፡

የግጥም ጥም፣ ሳልሳዊ አስፋው ከበደ

አማርኛ አባባሎች

  • የመኮንን ልጅ በከተማ የድሀ ልጅ በውድማ፤
  • ያንበሳ ልመና ጋማ ይዞ የቄስ ልመና አናዞ፤
  • ሀብታም በመመጽወቱ ድሀ በጸሎቱ፤
  • ካንጀት በላይ ፍቅር እያደር ያቃቅር፤
  • የሚውል ሆድ ማለዳ ይርበዋል፤
  • ለንፉግ ሰው የገበያ መንገድ ይጠበዋል፤
  • ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል፤

አማርኛ አባባል

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የህወሓት የቃላት ጦርነት ንሯል።ይዋጉ ይሆን?

ሶስቱም ኃይላት የጦር ኃይላቸዉን እያጠናከሩ፣ አዳዲስ ተዋጊ እየመለመሉ መሆናቸዉ...

የሐማስ ታጣቂዎች ከእስራኤል ጋር በመተባበር የተከሰሱ ሰባት ሰዎችን ገደሉ

ሰኞ እለት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ ያለ ቪዲዮ እንደሚያሳየው...