ከ27 ኪሎ ግራም ጥፍጥፍ ወርቅ በቁጥጥር ስር ዋለ

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ በቃሊቲ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ቱሉ ዲምቱ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በተደረገ ፍተሻ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 27 ነጥብ 75  ኪሎ ግራም ጥፍጥፍ ወርቅ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋለው ጥፍጥፍ  ወርቅ ከአንድ ወር በላይ ክትትል ሲደረግበት መቆየቱን የጉምሩክ ኮሚሽን የሕግ ተገዥነት ምክትል ኮሚሽነር አዘዘው ጫኔ ተናግረዋል፡፡

ጥፍጥፍ ወርቁን በህገወጥ መንገድ በተሽከርከሪ አካል ውስጥ ደብቀው ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሶስት ተጠርጣሪዎችና ሁለት ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡

የኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከፋና ዲጂታል

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢመማ 23ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስ አበባ እና በአዳማ ከተሞች ተካሔደ

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 23ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የመክፈቻው ሥነ_ሥርዓት...

ሐጅ ኡመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ...