ኩዊንስ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ከ4ሺ በላይ ተማሪዎቹን አስመረቀ። ተቋሙ ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል 1582 የሚሆኑት በቴክኒክ እና ሙያ የሰለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል።
በቅድመ ምረቃ መርሃ ግብር የተመረቁት ደግሞ 2620 ተማሪዎች እንደሆኑ ተጠቁሟል።
ተቋሙ በቅድመ ምረቃ መርሃግብር ያስመረቃቸው ተማሪዎች በአካዉንቲንግና ፋይናንስ እንዲሁም በማኔጅመንት ትምህርታቸውን የተከታተሉ እንደሆኑ ተገልጿል።
በቴክኒክ እና ሙያ መስክ የተመረቁት ደግሞ በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ፤ በማርኬቲንግ እና ሴልስ ማኔጅመንት፣ በሂዩማን ሪሶርስ ማኔጅመንት ሲክሬተሪ እና ኦፊስ አድሚኒስትሬሽን፣ በሃርድዌር እና ኔትዎርኪንግ ሰርቪስ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
በቀጣይ የሚሰጣቸውን የትምህርት ዓይነት ለማሳደግ እና ተደራሽ ለመሆን ማቀዱን የገለፀው ተቋሙ፤ ከዛ ባለፈም ወደ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለማደግ እንደሚሰራ ገልጿል።