( የትምህርት ጠኔ…..)
.
አፍሪካ ውሥጥ- የትምህርት ፖሊሢ እንደነከሠ ሞተር ነው።ለውጥ ወይንም ጥገና ያሻዋል።ያለሞተር ደግሞ መኪና – መኪና አይደለም። ያለትምህርት፣ያለሥልጣኔ፣ያለክህሎት….ሠው… ዘመን የዋጀ ሠብ አይሆንም። በሚጠቅምህ ትምህርትና ሥልጠና ላይ ግዜህን ኢንቨሥት አድርግ።
.
(የኔትወርክ ግጣም…..)
.
ኔትዎርካችሁን ፈትሹ – ‘ወርቅ ሃሣብህን አሥጥሎ ፋንድያ ከሚያሸክምህን ጀማ ተፋታ’ ዘመኑ ይህንን ይጠይቃል። ወደፊት ይጠቅመኛል የምትለውን ኔትዎርክ በእንክብካቤ ያዘው። በማይመለሡበት ከተማ በአህያ እየጋለቡ ይወጣል ይባላል።እዛ ከተማ የመጣ እንግዳ ባህያ መጋለቡ ነውር ሢሆን።
.
.
(የልብ ቀዶ ህክምና)
.
Dr Hafiz Mohammed ከኛ ጀማ ዋናው ነው።ክብሮአችን ነው ብዬያችኋለሁ አይደል?!
ከጀማችን ውሥጥ የልብ ቀዶ ህክምና እድሉን መሥጠት ላይ ተነጋግረንና -ከ3 እሥከ 5 ለሚሆኑ ህጻናት እና አዋቂ ታማሚዎች እና ኦፕሬሽኑን ለሚፈልጉ ግራንት(እድል ሠጥቶናል) አድርጎልናል። ለያንዳንዱ ታካሚ በአማካይ ከ 700,000 ብር እሥከ 800,000 ብር የሚያወጣ እገዛ ተዘጋጅቷል።
.
(ጀማው…..)
.
ይህንን ህክምና ለሚያሥፈልጋቸው እና ለመታከም አቅሙ ለሌላቸውን በተለይ ህጻናትን ይምረጥ።….ባሥቸኳይ ሃዋሣ ሆሥፒታል ሄደው screen ይደረጉ፤ዶኪዩመንታቸውን በቀጥታ ለ Tazma medical and surgical specialized center ይላኩ። እዚህ ላይ ይህንን አገልግሎት ለማግኘት ለሚፈልጉ እዚሁ ምረጡ እና እንልካለን።
ቪዲዮውን ከልሙት እሥኪ።
በርቱ!
Bejai Nerash Naiker
