የሒሳብ ባለሙያዎችና የውጭ ኦዲተሮች ቁጥጥር

Date:

የሒሳብ ባለሙያዎችና የውጭ ኦዲተሮች በተሰጣቸው የሙያ ፈቃድና ዓለም አቀፍ የአሠራር ደረጃዎች መሠረት እየሠሩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ እየተቆጣጠረ መሆኑን አስታወቀ።

የቦርዱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈቃዱ አጎናፍር፤ ቦርዱ በአዋጅ ቁጥር 847/2006 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሙያ ፈቃድ ከመስጠት ባለፈ ባለሙያዎቹ በፈቃዳቸው መሠረት በአግባቡ እየሠሩ መሆናቸውን የመከታተልና የመቆጣጠር ኃላፊነት እንዳለው ገልጸዋል።

በሀገሪቱ ወጥ የሒሳብ አሠራር ሥርዓት ለመዘርጋት ቦርዱ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና የኦዲት ደረጃዎችን ተቀብሎ እያስተገበረ መሆኑንም አስታውቀዋል።

የድርጅቶችን ትክክለኛ የገንዘብ አቅምና ሀብት ለማወቅ በደረጃው መሠረት የተዘጋጀና የተመረመረ የሒሳብ መግለጫ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው፤ በተሳሳተ መንገድ የቀረበ የሒሳብ ሪፖርት ባንኮችንና ሌሎች ውሳኔ ሰጪ አካላትን ለተሳሳተ ውሳኔ ሊዳርግ እንደሚችል አስገንዝበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ነገ በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመጪው ሐሙስ ህዳር 17...

ከፍተኛ የወጪ ንግድ ገቢ ያስመዘገቡ ድርጅቶች ተሸለሙ

በጥራጥሬና ቅባት እህሎች ዘርፍ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ገቢ ያስገኙ...

ዓለም አቀፉ ሽልማት ለጋዜጠኛ ይስሐቅ በላይ ተሰጠዉ

ዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ (IOC) በ4ኛው የዓለም የወጣቶች ኦሎምፒክ...

የተመድ ዋና ፀሐፊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስጋቶችን ለመቆጣጠር ዓለም አቀፍ ትብብር ጠየቁ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ፣ የሰው ሰራሽ...