የማሌዥያ በአዲስ አበባ የሚገኘውን ኤምባሲ ከ43 ዓመታት በኋላ ተከፈተ

Date:

ማሌዥያ በአዲስ አበባ የነበራትን ኤምባሲ ከ43 ዓመታት በኋላ ዳግም በይፋ ከፈተች።

የማሌዥያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  መስከረም 19 ቀን 2018 ባወጣው መግለጫ፣ ኤምባሲው ከ መስከረም 13  ቀን 2018 ጀምሮ ሥራ መጀመሩን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን  እንደገለጹት፣ ማሌዥያ በአውሮፓውያኑ 1982 ዓ.ም. ከነበረው የደርግ ሥርዓት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷ በመሻከሩ ምክንያት ኤምባሲዋን ዘግታ ነበር።

የማሌዥያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው፣ “የኤምባሲው ዳግም መከፈት ማሌዥያ ከኢትዮጵያ ጋር  የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።

እንዲሁም፣ በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ፣ የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያስገኙ የትብብር ዘርፎች አዳዲስ ዕድሎችን ለማሰስ  ይረዳል” ብሏል።

መግለጫው አክሎም፣ የአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ የኤምባሲው ዳግም መከፈት፣ ከአኅጉራዊው ተቋም ጋር ለመሥራት አዳዲስ መንገዶችን ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ገልጿል። ኤምባሲው ለጊዜው ሥራውን እያከናወነ ያለው በሸራተን አዲስ ሆቴል ውስጥ በሚገኝ ጊዜያዊ ጽህፈት ቤት ውስጥ ነው ተብሏል።አስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ዕጣ ፈንታቸው ወደ ኤሌክትሪክ መቀየር ነው

በነዳጅ የሚሠሩና አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ተሽከርካሪዎች ዕጣ ፈንታቸው ወደ...

ህጻናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ተመረቀ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚሰሩ የልማት ሥራዎች ሁሉ ኪነ...

ትራምፕ ውሸታም ናቸው- የኮንግረስ አባል ኢልሀን

የኮንግረስ አባል ኢልሀን ኡመርና የፕሬዝደንት ትራምፕ ውዝግብ እንደቀጠለ ነው፡፡...

የአውሮፓ ህብረት አመነ

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን የኮቪድ ክትባት ትክክለኛ የጤና ቁጥጥር ሂደቶችን...