በከተማው ተነስቶ በነበረው ግጭት ከፀጥታ አካላት በተተኮሰ ጥይት የሶስት ሰዎች ሕይወት አልፏል

Date:

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጀራ ከተማ በመስቃን ወረዳ እንቦር ቀበሌ ስር ይተዳደርበት የነበረ የስናኖ ሴራ የተባለ አካባቢን የዞኑ ስራ አስፈፃሚ አካላት ” የዶቢ ቀበሌ ነው ” ማለታቸዉን ተከትሎ ተቀሰቀሰ በተባለው ሁከት ከፀጥታ አካላት በተተኮሰ ጥይት የ3 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የቡታጅራ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

አንድ ማንነቱ እንድንገለፅ ያልፈለገ የከተማው ነዋሪና የዐይን እማኝ እንደገለፁት በከተማው ከብራይት ወደ መድረሳ ሰፈር በሚወስደው መንገድ ላይ በተለምዶ አደባባይ ሰፈር አንዲት ሴት  በአንድ አድማ በታኝ በተተኮሰ ጥይት  መገደሏን መመልከቱንና ተኳሹ በቡታጅራ ከተማ በሚገኘው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና ኮንስትራክሽን ቢሮ አከባቢ እንደነበር ተናግሯል።

” ሌላ ወጣት የተገደለው በትክክልና በተነጣጠረ ጥይት ነው ” ሲሉ ሌላኛው የከተማው ነዋሪ ገልጿል።

አጠቃላይ የነበረው እንቅስቃሴ ችግሩን የሚያባብስ እንደነበር አክለዋል።

አንድ ታዳጊ፣ አንዲት ሴትና አንድ ወጣት በአጠቃላይ 3 ሰዎች መገደላቸውን የገለፁት ነዋሪዎቹ በርካቶችም በሁከቱ መቁሰላቸውንና ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ሙሰማ ጀማል አነጋግሯቸዋል።

ስለሁኔታው ሰፊ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዉ ሁከቱን በመቀስቀስና በማስተባበር እንዲሁም በመምራት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ ከተማው ወደ ቀደመ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱንና ሌሎች መረጃዎችን በሌላ ጊዜ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።

አንድ የአከባቢዉ የመንግስት የስራ ኃላፊ የአመፁ መንስኤ የሆነው የመስቃን ጉራጌ የእንቦር ቀበሌ ባህላዊ የአስተዳደር ሴራ የሆነውን የስናኖ ሴራ ህዝቡ ባልተወያየበትና የወረዳው ምክር ቤት ባላፀደቀበት የዞኑ ስራ አስፈፃሚዎች ” የባህል ሴራው የመስቃን ጉራጌ የእንቦር ቀበሌ ሴራ አይደለም የዶቢ ቀበሌ ሴራ ነው ” በማለት መወሰናቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ይህን ተከትሎም ከህዝቡም የተመረጡ ሽማግሌዎች በተደጋጋሚ ” ይሄ የባህል ቅሚያ ትክክል አደለም ህዝቡን ወዳልሆነ መንገድ ይመራዋል አስቁሙ ፣ ህዝቡን አወያዩ ” ቢሉም የዞኑ ስራ አስፈፃሚ ጉዳዩን በቸልተኝነት ማየቱ ችግሩ እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል ብለዋል።

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...