የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ማህበርበኢትዮጵያ መግለጫ አውጥተዋል

Date:

የወጣዉ ምስል የምንሸማቀቅበት ሳይሆን ሁሌም ደረታችንን ነፍተን በኩራት የምናሳየው ምስል ነው ።

እንደሚታወቀው እኛ የማንችስተር ደጋፊዎች እንደ ማህበር ከተሰባሰብን ስምንት አመት አልፎናል በዚህ ስምንት አመት ውስጥ እግር ኳስን ለመልካም ስራ በመጠቀም ቀዳሚዎች ነን።

በመሰባሰባችን ምክንያት ላለፉት ተከታታይ ስምንት አመት ያለማቋረጥ የመማሪያ ቁሳቁስ አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች በመስጠት ከትምህር ገበታቸው እንዳይቀሩ ምክንያት ሆነናል።

የደም ልገሳ ለ19ኛ ጊዜ በመለገስ የወገኖቻችንን ህይወት ከፈጣሪ በታች አስቀጥለናል ሌላው በየአመቱ በጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል እና በዘውዲቱ የእፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ለሚገኙ ወገኖቻችን  የምናደርገው የምግብ ማብላት ፕሮግራም ተጠቃሹ ነው ።

ይሄ ሁሉ የሆነው በመልካምነት ስራቸው ሀገር በሚያቃቸው በማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች እና እግር ኳስ አንድ ባደረጋቸው የተለያዩ ክለብ  ደጋፊዎች ምክንያት ነው ለዚህም መልካምነታቹ ከልብ እያመሰገንን

ከትላንቱ የክለባችን ጨዋታ በዋላ በማህበራዊ ሚድያ እየተዘዋወረ ሀሰተኛ መረጃ እየተሰራበት እና ለመበሻሸቂያ በማይሆን ምስል ላይ ይሄን ማለት እንወዳለን።

ይሄ ምስል በየአመቱ እንደምናደርገው በ 2015 ላይ በጌርጌሴኖን ተገኝተን በማዕከሉ ለሚገኙ ወገኖች የምገባ ፕሮግራም ስናደርግ የተነሳ ምስል ነው አንዳንዶች  እንደሚሉት ከጨዋታው በዋላ የተቸገሩትን ሊመግቡ የነበረውን በመሸነፋቸው ምክንያት ሰረዙት በማለት የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ ይገኛሉ።

እኛ የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ውጤት ጠብቀን አደለም የመልካምነት ስራ የምነስራው በዚ ተሸማቀን የመልካም ስራችን ለሰከንድ አናቋርጥም ውጤት ጠብቀን መልካምነት እንደማንሰራ ባለፉት ስምንት አመታት በሚገባ በተግባር ላሳየ ደጋፊ በዚ ምስል ለማብሸቅ መሞከር ሞኝነት ነው የዘንድሮም የምሳ ማብላት ፕሮግራማችንን በማዕከሉ ለሚገኙ 655 ወገኖች ሚያዚያ 26 / 2017  ማከናወናችን ይታወቃል ።

በተጨማሪ ከታች ያለውን ፎቶ በተለያዩ መንገድ ለመበሻሸቂያ እየተጠቀማቹ   ያላችሁ በማዕከሉ ውስጥ ለሚገኙ ስትሉ ከድርጊታቹ እንድትቆጠቡ እንጠይቃለን።
@ የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ማህበር በኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ቃል አቀባይዋ ዩክሬን የአፍሪካ ሀገራትን መበቀል ትፈልጋለች አሉ

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፣ ኪዬቭ የአፍሪካ አገራት...

ሕጻኑ በሀገሪቱ የመጀመሪያ በሆነ ቀዶ ሕክምና ተወለደ

የ28 ዓመቷ ወይዘሮ ሰናይት ታምራት ቀደም ሲል በነበረው እርግዝናዋ...

ግብፅ የኤርትራን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እንዲከበር ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች

የግብፅ ፕሬዝዳንት አብድል ፈታህ አልሲሲ፤ የኤርትራን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት...