የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ የሀገር ሉዓላዊነት ጉዳይ ነዉ

Date:

የሳይበር ደህንነት ጉዳይ ከሀገር ሉዓላዊነት ጋር የሚተሳሰር መሆኑን በመገንዘብ በዘርፉ የሚከናወኑ ቅንጅታዊ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለም ፀሐይ ጳውሎስ ገለፁ።

6ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ማስጀመሪያ ስነ ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ ባስተላለፉት መልእክት ባለፉት የለውጥ ዓመታት በሁሉም ዘርፎች ስኬታማ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል።

የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጅማሮ ማሳያ የሆኑ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ የተመረቁና የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መንግስት ለዘላቂ ልማትና እድገት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳዩ ናቸው ብለዋል።

የዜጎችን የዕለት ተዕለት የህይወት እንቅስቃሴና የመንግሥትን አገልግሎት የሚያሳልጡ የዲጂታል አሠራሮችን በመተግበር ተጨባጭ ለውጦች መምጣታቸውን አንስተዋል።

በአሁኑ ወቅት ከ900 በላይ የሚሆኑና በተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ አማካይነት ለተገልጋዮች ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ቴክኖሎጂና ልማት ተሰናስለው የሚሔዱ ናቸው ያሉት ሚኒስትሯ፥ የልማት ስራዎቹ ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲቆይ ማድረግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።

የሳይበር ደህንነት ጉዳይ ከሀገር ሉአላዊነት ጋር የሚተሳሰር በመሆኑ በዘርፉ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

NBC Ethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የህዳሴ ግድቡ ውዝግብ በፖለቲካዊ ሳይሆን በቴክኒካዊ መንገድ መፈታት አለበት

በአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ፣ እና የመካከለኛው ምስራቅ...

የ7 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ አለመከናወኑ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሚተዳደሩ 7 የጋራ መኖሪያ...

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ በ80 ዓመታቸው ከዚህ...