የሶሪያ ፕሬዚዳንት አህመድ አል ሻራ በህዳር ወር መጀመሪያ ላይ በአሜሪካ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ በዚህም አሜሪካን የሚጎበኙ የመጀመሪያው የሶሪያ መሪ እንደሚሆኑ ተነግሯል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በአሜሪካ በሚያደርጉት ጉብኝት በሶሪያ መልሶ ግንባታ ዙሪያ እንደሚወያዩ ተዘግቧል፡፡
ጉብኝቱ በሶሪያ ላይ ተጥለው የቆዩ ማዕቀቦችን ለማንሳትና በአሜሪካና ሶሪያ ግንኙነት መካከል አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት ያስችላል ነው የተባለው፡፡
በሁለቱ ሀገራት መካከል በጣም ጠንካራ አጋርነት መመስረት እንፈልጋለን ያለው የሶሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ የፕሬዚዳንት አህመድ አል ሻራ ጉብኝት ይህን ለማሳካት ወሳኝ መሆኑን ገልጧል፡፡
