የኃይሉ አመርጋ አልበም የሚለቀቅበት ቀን ታወቀ

Date:

ድምጻዊ ኃይሉ አመርጋ ከተራራው ማዶ፣ እንግዳ፣ ይነጋል፣ ማርዬ፣ ይገርማል የተሰኙ ሙዚቃዎችን ጨምሮ አስር ያህል ሥራዎችን በጃኖ ባንድ በኩል መዋጮ አድርጎ።

ከጃኖ ባንድ ባንድ መፈርስ በኃላ ከኃይሉ አመርጋ በቀር 3ቱ የባንዱ ድምጻዊያን በየፊናቸው የራሳቸውን የሙዚቃ  አልበም ለአድማጮች አቅረበዋል።

በሙዚቃ ወዳጆችም ዘንድ የኃይሉ አመርጋ የሙዚቃ አልበም መቼ  ነው የሚለቀቀው የሚሉ ጥያቄዎች ለድምጻዊው ሲቀርቡ ቆይተዋል።

ለዚህም ጥያቄ በመጨረሻም አልበሙ ለአድማጮች የሚቀርብበት ቀን ታወቋል።

ድምጻዊው በግሉ የሰራው የመጀመሪያ አልበሙ ጥቅምት 21 2018 ዓ.ም ለአድማጮች እንደሚቀረብ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከድምጻዊው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የአልበሙን ስራ ለመከውን ስድስት ዓመታት እንደፈጀ የተነገረለት አልበሙ “አሁን ” የተሰኘ ርዕስ ተሰጥቷል።

ከመለቀቁ በፊትም ጥቅምት 18 2018 ዓ.ም የሙዚቃ ማድመጭ መሰናድ እንደተዘጋጀለትም ሰምተናል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ለሊት እንቅልፍ የለኝም

"አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ያሳስበኛል፤ እኔ አሁን 86 ዓመት...

አዎ ነበሩ ….

🔘የሁሉም አባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሓጅ ዑመር🔘ነፍስዎ በሰላም ትረፍ "...

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን ሳር ቅጠሉ የሚወዳቸው

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን ሳር ቅጠሉ የሚወዳቸው የሀይማኖት...