የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥትበ በአርሲ የተፈጸሙ ግድያዎች በፅኑ እንዳሳሰበው ገለፀ። ግድያዎች በአግባቡ ተጣርተው ጥፋተኞች ለሕግ እንዲቀርቡም ጠይቋል።
በአርሲ በተፈጸመ ጥቃት ከ 60 በላይ ንፁሐን ዜጎች መገደላቸው መዘገቡ ይታወሳል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ ባወጣው መግለጫ፤ ዩናይትድ ስቴትስ በሃይማኖት፣ በጎሳ ወይም በፖለቲካ ተነሳስተው የሚፈጸሙ ጥቃቶችን አጥብቃ ታወግዛለች» ብሏል።
መግለጫው አክሎም በየትኛውም ቡድን ላይ የሚፈጸሙ እንዲህ ያሉ አሰቃቂ ጥቃቶችመቆም እንዳለባቸውም አሳስቧል። ድርጊቱዩናይትድ ስቴትስን በእጅጉ ያሳሰባት መሆኑን የገለጸው መግለጫው አጥፊዎች ለሕግ ይቅረቡ ብሏል።
አሳዛኙን ድርጊት ለመረዳት ጥረት እያደረገ መሆኑን ያመለከተው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ፤ መከፋፈል ይበልጥ ስር እንዲሰድ ከሚያደርጉ ፍረጃዎች ጥንቃቄ እንዲደረግም ጠይቋል።
መግለጫው አክሎም ዋሽንግተን፤ አስፈላጊውን ምርመራ በማካሄድ ጥፋተኞችን በተጠያቂነት መያዛቸውን እንዲያረጋግጥ ለኢትዮጵያ መንግስት ጥሪ ማቅረቡን ገልጿል።
