በስፖርት ጋዜጠኝነት ለበርካታ ዓመታት የሠራው የአባይ ቲቪ ጋዜጠኛ ዮሴፍ ከፈለኝ በኩላሊት ህመም ምክንያት ሕክምና እየተከታተለ መሆኑ ተገለጸ።
ጋዜጠኛው በሕክምና ተቋም በመተኛትና በተመላላሽ ሕክምና እየታከመ ሲሆን፣ ለሕክምናው ከፍተኛ ወጪ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። ሕክምናው እስከ ኩላሊት ንቅለ ተከላ ሊደርስ እንደሚችልም በቀረበው የድጋፍ ጥሪ ተመልክቷል።
ዮሴፍ በሀገር ውስጥ ስፖርትና በስፖርት ጋዜጠኝነት ሙያ ላይ የራሱን አስተዋጽኦ ያበረከተ ባለሙያ መሆኑን በመጥቀስ፣ ለሕክምናው የሚያግዝ የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግለት ጥሪ ቀርቧል።
የድጋፍ ገንዘቡ በባለቤቱ ወ/ሮ ብርሃን በኩረፅዮን ስም በሚገኘው የኢንተርናሽናል ንግድ ባንክ (ኢ/ን/ባንክ) ሂሳብ ቁጥር 1000729159895 እንዲገባ ተገልጿል
