የአትሌት ፋንታዬ ጥሩ ዕድል

Date:

አትሌት ፋንታዬ በላይነህ ትናንት ምሽት የዙሪክ ዳይመንድ ሊግ ፍፃሜ በ3000 ሜትር ማሸነፏን ተከትሎ ለቶኪዮ የዓለም ሻምፒዮና በWild Card በቀጥታ ማለፏን አረጋግጣለች።

የዓለም አትሌቲክስ አዲስ ባወጣው ህግ መሰረት ቀደም ሲል ለሻምፒዮናው ሚኒማ ያላሟሉ ወይም ሚኒማ ኖሯቸው በሌሎች አትሌቶች በመበለጣቸው ምክንያት በሀገራቸው ብ/ቡድን መካተት ያልቻሉ አትሌቶች በዳይመንድ ሊጉ ፍፃሜ ካሸነፉ በቀጥታ በWild Card እንዲያልፉ ወስኗል።

ፋንታዬ በላይነህ የዛሬ ድሏን ተከትሎ የቶኪዮ ቲኬቷን መቁረጥ ችላለች። በዚህም መሰረት በዓለም ሻምፒዮናው በ5000 ሜትር ትወዳደራለች። ምክንያቱም በዓለም ሻምፒዮና የሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል እንጂ የቀጥታ ውድድር የለም። በ5000 ሜትር  የተሳታፊ አትሌቶቻችንም ቁጥር ወደ አራት ከፍ ብሎልናል።

አሁን ሁሉም ነገር ተጠናቅቋል…ሙሉ ትኩረታችን የቶኪዮ የዓለም ሻምፒዮና ይሆናል!!

መልካም ዕድል ለጀግኖች ለአትሌቶቻችን!!

ምስጋናው ታደሰ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከጥር 1 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ለጫት ላኪዎች የቅድመ ፈቃድ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መስጠት ይቆማል

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከጫት ወጪ ንግድ ፈቃድና የብቃት...

ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞች ይፈለጋሉ

በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች መኖራቸውንና...

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ ሪፖርትን እስከ ነገ በቅጣት እንደሚቀበል አስታወቀ

  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር...

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...