የአቶ ታዬ ጠበቃ ችሎቱ “በስውር ነው የተካሄደው” ሲሉ ከሰሱ

Date:

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደአ የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ጉዳያቸውን ማረሚያ ሆነው እንዲከታተሉ ትዕዛዝ መስጠቱን ጠበቃቸው ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።

እንደ ጠበቃው ገለፃ አቶ ታዬ ዛሬ ግንቦት 26/ 2017 ከቀኑ 6 ሰዓት አካባቢ ያለ ጠበቃ “በስውር” ወደ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። “ያለ ጠበቃ ነው ችሎት የቀረቡት” ያሉት ጠበቃው፤ እንደነዚህ ያሉ ጉዳዮች የሚከናወኑት በተከሳሹ ጠበቃ ወይም በፍርድ ቤት በተሰየመ የህዝብ ጠበቃ ፊት ብቻ ነው፤ ነገር ግን ይህ መስፈርት ተጥሷል” ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ችሎቱ የተካሄደው በምሳ ሰዓት መሆኑን በመግለጽ “በተለምዶ ፍርድ ቤት ሂደቶች የማይካሄድበት ጊዜ ነው” በማለት ገልፀዋል። ጠበቃው ችሎቱ በተለይ ዋስትናቸውን ለማንሳት በስውር የተዘጋጀ ይመስላል” ሲሉ ገልጠዋል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ላይ የተመሰረቱ ሁለት የወንጀል ክሶችን ወደ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመመለስ በድጋሚ ክርክር አንዲደረግባቸው ትዕዛዝ ከተላለፈባቸው ከጥቂት ሰአታት በኋላ ከመኖሪያ ቤታቸው በትናንትናው ዕለት ተወስደዉ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የቀደሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታው ከቀረቡባቸው ሦስት ክሶች መካከል ሐምሌ 30/ 2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት በ1ኛ እና በ2ኛ ክስ ነጻ የተባሉ ሲሆን የጦር መሳሪያ ወንጀሎችን በተመለከተ የቀረበባቸውን ሶስተኛው ክስ ተለቀው እንዲከላከሉ ብይን መሰጠቱም ይታወሳል፡፡

አቶ ታዬ ላይ ነፃ የተባሉበት ሁለቱ ክሶች “ከጠላት ጋር በመተባበር” እና “የፀረ-ሰላም ቡድኖች የሆኑትን ሸኔ እና ፋኖን የሚደግፉ መልዕክቶችን” በፌስቡክ ገፃቸው አጋርተዋል ከሚሉት ክሶች ነበር።

ይህን ተከትሎም አቶ ታዬ ህዳር 23 ቀን 2016 በዋለው ችሎት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በዋስትና እንዲፈቱ ተወስኖ ህዳር 26፣ 2016 ዓ/ም ከእስር ቤት ወጥተው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ ነበር።

ይሁን እንጂ አቃቤ ህግ አቶ ታዬ ከተመሰረተባቸው ሁለቱ ክሶች ነፃ መባል የለባቸውም በሚል ይግባኝ በማለቱ ጉዳዩ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቷል።

በጉዳዩ ላይ ትናንት ውሳኔ የሰጠው ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግን ይግባኝ በማጽናት አቶ ታዬ ነፃ በሆኑበት ሁለቱ ክሶች እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል።

በመሆኑም ክሶቹ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደሚመለሱና ክርከሩ የሚቀጥል ሲሆን፤ የዋስትና መብታቸውም ተነስቶ ጉዳያቸውን ማረሚያ ሆነው እንዲከታተሉ በዛሬው ዕለት ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ የመከላከያ ምስክርን ለመስማት ለሰኔ 30 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። አስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

‹‹ኢሳያስ አፈወርቂ ከአገር ይኮበልላሉ››

የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር ሻብያን ነክሰው ይዘዋል፡፡ ዛሬ ደግሞ፣ ፕሬዝዳንት...

የቀድሞው የዶናልድ ትራምፕ አማካሪ ጆን ቦልተን ተከሰሱ

ጆን ቦልተን በሪፐብሊካኑ የመጀመሪያው ዙር የፕሬዚዳንትነት ወቅት የብሄራዊ ደህንነት...

“ወደራስ መመለስ!”

በ99ኛ የስብሐቲዝም መድረክ ከፍልስፍና መምህሩና ጋዜጠኛ ደረጀ ይመር ጋር...