የኢትዮጵያ መንግሥት ክስና ህወሓት

Date:

 በኢትዮጵያ ላይ  ጦርነት ሊከፍቱ እየተዘጋጁ ነው በሚል ከኤርትራ መንግሥት ጋር የከሰሰችው ህወሓት ከኤርትራ ጋር የተጀመረው ግንኙነት የህዝብ ለህዝብ መሆኑ ሲገልፅ ቆይቷል።

በቅርቡ ህወሓት ባካሄደው የትግራይ ብሔራዊ ኮንፈረንስ የተባለ መድረክ በአፍሪቃ ቀንድ ያንዣበበውን አደገኛ ጦርነት በሩቅ ለማስቀረት በጋራ እንስራ የሚል ጥሪ ለኤርትራ ህዝብ ተላልፏል።

ህወሓት እና የኤርትራ መንግስት በተመለከተ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተባበሩት መንግስት ዋና ፀሓፊ የፃፈው ደብዳቤ የበርካቶች መወያየት አጀንዳ ሆኖ ይገኛል።

በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ለቀረቡ ክሶች ህወሓት በቀጥታ ምላሽ ባይሰጥም፥ በተለይም በአማራ ክልል ላሉ ታጣቂዎች ድጋፍ ያደርጋል ተብሎ ለሚቀርብ ክስ የትግራይ ሐይሎች ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ሲያጣጥሉት ቆይተዋል። 

የትግራይ ሐይሎች ተሳትፎ

ከትግራይ ወታደራዊ አዛዦች መካከል የሆኑት ጀነራል ዮሃንስ ወልደጊዮርጊስ በቅርቡ በሰሜን ወሎ በነበረ ሁኔታ የትግራይ ክልልኃይሎች ተሳትፎ አለመባሉ በማጣጣል፣ የትኛው ሐይል ከየት ተነሳ ወዴት አመራ የሚል ለማወቅ በዚህ ዘመን ቀላል ሆኖ ሳለ ይሁንና ትግራይን ለመወንጀል በመፈለጉ ብቻ ውንጀላው መቅረቡ ጀነራል ዮሃንስ ከክልሉ ፀጥታ ሐይሎች ጋር ባደረጉት ውይይት ሲናገሩ ተደምጠዋል።

 በሌላ በኩል በኤርትራ እና ትግራይ መካከል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መጀመሩ በማንሳት ይህም ህወሓት እንደሚደግፈው በተደጋጋሚ ሲገልፅ የቆየ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ባደረግ ትልቅ መድረክም ይህ ግንኙነት የሚያሳድግ ሁኔታ እንዲፈጠር ጥሪ የሚያቀርብ መልእክት ተላልፏል። 

ጥሪ ለኤርትራ

ህወሓትባካሄደው እና ‘የትግራይ ህዝባዊ ኮንፈረንስ’ በተባለ መድረክ ማጠቃለያ የተሳታፊዎች የአቋም መግለጫ ተብሎ ለኤርትራ ጥሪ ቀርቦ የነበረ ሲሆን በትግራይ እና ኤርትራ ህዝቦች ላይ ያነጣጠረ የጦርነት አደጋ አንዥቦ እንዳለ ያነሳል።

እሁድ በተጠናቀቀው መድረክ በንባብ የቀረበው የአቋም መግለጫ በአፍሪካ ቀንድ አንዣቦ ያለው ጦርነት ለማስቀረት በጋራ የመስራት ጥሪ የሚያቀርብ ሲሆን የኤርትራ ህዝብ ለዚህ ሚናው እንዲወጡ ጥሪ ያቀርባል።

ከትግራይ ሐይሎች ተለይተው ራሳቸው በአፋር እያደራጁ ካሉ ታጣቂዎች መካከል፥ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ጥሪ ተቀብለው የተመለሱ ከተባሉ ወጣቶች ጋር ትላንት ውይይት ያደረጉ የትግራይ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሐላፊ ጀነራል ፍስሃ ኪዳኑ ባሰሙት ንግግር የኢትዮጵያ መንግስት የሰላም መንገዶች ዝግ እያደረገ ነው በማለት ከሰዋል።

የሰላም ውሉ 

የሰላም ውል ከተፈረመ ሶስት ዓመት ቢያልፍም ለትግራይ ጥያቄዎች ምላሽ አልተሰጠም፣ የትግራይ ውክልና በፌደራል መንግስቱ የለም ያሉት ጀነራሉ፥ በተቃራኒው ትጥቃችሁ ፍቱ፣ ተቋማቶቻችሁ አፍርሱ የሚሉ ግፊቶች እየተደረጉ እየተደረጉ እንዳሉ እና ተቀባይነት እንደሌላቸው አመልክተዋል።

ጀነራል ፍስሃ “ሉአላዊ ግዛታችን ይመለስ፣ መንግስት ይኑረን፣ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ተቋማት ውእልና እንዳይኖረን እያደረጋችሁ ነው እያልን ነው።

ሶስተኛ ዓመት እያደረግን ነው ለዚህ ምላሽ የለም፥ ታድያ ችግሩ እንዴት ነው የሚፈታው ? ሰላም የሚያመጡ መንገዶች የኢትዮጵያ መንግስት ዘግቶ ይዞ ይገኛል። . . .  ትጥቃችሁ አውርዱ፣ አደረጃጀታችሁ አፍርሱ እና ከዛ በኃላ ከፈለጋችሁ ተገንጠሉ ከፈለጋችሁ ሂዱ ሲሉን አያሳፍርም ወይ ? እነዚህ ሰዎች የትግራይ ህዝብን በሚገባ ያወቁት አይመስለኝም” ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በህወሓት እንዲሁም አጠቃላይ የትግራይ አመራሮች እየተደረገ ያለው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ‘አንድነት በማጠናከር፥ ጦርነት በሩቅ ለማስቀረት’ ያለመ መሆኑ የትግራይ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሐላፊ ጀነራል ፍስሃ ኪዳኑ ጨምረው ተናግረዋል።

ጀነራሉ “አንድነታችን አጠንክረን ይዘን ጦርነት እና የጦርነት ወሬ የሚጠፋበት፥ ችግሮች በሰላም እና በውይይት የሚፈታበት ሁኔታ መፈለግ ነው” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት በፃፈው ደብዳቤ ዙርያ እስካሁን ከህወሓት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፥ በጉዳዮም እስካሁን የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ የለም።

DW Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የህዳሴ ግድቡ ውዝግብ በፖለቲካዊ ሳይሆን በቴክኒካዊ መንገድ መፈታት አለበት

በአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ፣ እና የመካከለኛው ምስራቅ...

የ7 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ አለመከናወኑ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሚተዳደሩ 7 የጋራ መኖሪያ...

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ በ80 ዓመታቸው ከዚህ...