የከተማዋ የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመቀነስ ከአራት መቶ በላይ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን የመጠገንና የማፅዳት ስራ መሰራቱ ተገለፀ

Date:

መጪው የክረምት ወቅትን ተከትሎ በከተማዋ የጎርፍ አደጋ እንዳይከሰት የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን የመጠገንና የማፅዳት ስራ መሰራቱን የከተማዋ የመንገዶች ባለስልጣን ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልጿል፡፡

በ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በርካታ የመንገድ ግንባታ እና ጥገና መከናወኑን የገለፁት የአዲስ አበባ መንገዶችን ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ናቸው፡፡

ባለፉት ወራት በተለያዩ አካባቢዎች 835 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የመንገድ ጥገና መደረጉን እና በጀት የተመደበላቸው የመንገድ ግንባታዎች መከናወናቸውን አመላክተዋል፡፡

ባለስልጣኑ በየአመቱ የጎርፍ ስጋትን ለመቀነስ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን የማፅዳት ስራ ተቋሙ ቢሰራም ማህበረሰቡ አሁንም ደረቅ ቆሻሻን ወደ ፍሳሽ ማስወገጃ በመጣል ስጋቱ እንዲኖር እያደረገ መሆኑን አመላክተዋል፡፡በዚህም በጎርፍ ምክንያት የተጠገኑ መንገዶች ዳግም እንዲበላሹ ምክንያት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ባልስልጣኑ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባባር ፍሳሽ ማስወገጃዎቹ በድጋሚ እንዳይደፈኑ ለማድረግ የቁጥጥር ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የከተማዋ የመንገዶች ባለልስጣን ባለፉት ዘጠኝ ወራት ግንባታውም የተጠናቀቁ እንዲሁም በቀጣይ አመት ለአገልግሎት ክፍት የሚሆኑ የመንገድ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን ገልጿል፡፡

menahriafm

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ለሊት እንቅልፍ የለኝም

"አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ያሳስበኛል፤ እኔ አሁን 86 ዓመት...

አዎ ነበሩ ….

🔘የሁሉም አባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሓጅ ዑመር🔘ነፍስዎ በሰላም ትረፍ "...

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን ሳር ቅጠሉ የሚወዳቸው

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን ሳር ቅጠሉ የሚወዳቸው የሀይማኖት...