የካናዳ ከፍተኛውን የክብር ሽልማት ያሸነፈችው ኢትዮጵያዊት

Date:

ከኢትዮጵያ ተነስታ በካናዳ በስደት ትኖር የነበረችው መሠረት ሀይለየሱስ፣ በካናዳ ለሴቶች እኩልነት በሚደረገው ትግል የሚሰጠውን ከፍተኛ ክብር የ”Governor General’s Award” ሽልማት አሸናፊ ሆናለች።

ላለፉት 10 ዓመታት በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ ያለፈችው መሠረት፣ በካናዳ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን የገንዘብ ቁጥጥር በደል (Financial Abuse) የሁሉም ትኩረት እንዲሆን በማድረጓ ለብዙ ስደተኞችና ሴቶች ትልቅ አርአያ ሆናለች።

መሠረት ይህንን ችግር ወደ ብሔራዊ ደረጃ በማምጣት የመጀመሪያዋ ሴት ለመሆን የበቃች ሲሆን፤ ህዳር 26 በካናዳ “የኢኮኖሚያዊ በደል ግንዛቤ ቀን” ሆኖ እንዲከበር አድርጋለች።

ይህ ጥረቷ በካናዳ ምክር ቤትና ከ100 በላይ ማዘጋጃ ቤቶች እውቅና ያገኘ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ወደ 5 ሀገራት ተስፋፍቷል። በተጨማሪም በኢንተርኔት ገንዘብ ማስተላለፍ (e-transfer) ላይ የደህንነት ማሻሻያዎች እንዲደረጉና በባንኮችና በፖሊሲዎች ላይ ለውጥ እንዲመጣ ትልቅ ድርሻ ተወጥታለች።

በስራዋም ከ100,000 በላይ ሰዎችን፣ 22 የገንዘብ ተቋማትን እና 356 ድርጅቶችን ማንቀሳቀስ የቻለች ሲሆን፣ በካናዳ ፓርላማና ሴኔት በመቅረብም ምስክርነት ሰጥታለች።

እነዚህንና በርካታ አገራዊ አስተዋጽኦዎችን በማበርከቷም ይህንን ታላቅ የካናዳ መንግስት የክብር ሽልማት ልትጎናጸፍ ችላለች።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ሹመት

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ሌ/ጄኔራል በላይ...

የብፁዕ አቡነ ሉቃስ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ

  የሥርዓተ ቀብር መረጃ:- የሰቲት ሁመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት...

የዛሬ ዘጠኝ ጨዋታዎች

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ3ኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት...

በ20 ሚሊዮን ብር የተገዛ የእንስሳት መድኃኒት የጥራት ችግር ነበረበት

በግዢ ሂደት ውስጥ በተደረጉ ማሻሻያዎችና የላቦራቶሪ ማረጋገጫዎች የከፋ የጥራት...