የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገት በ2026 ቅናሽ እንደሚያሳይ ተተነበየ

Date:

የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገት በ2026 ቅናሽ እንደሚያሳይ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም(አይ.ኤም.ኤፍ) ትንበያ አዲስ ባወጣው ትንበያ አመላክቷል። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም(አይ.ኤም.ኤፍ) ሀገራት በ2026 የሚያስመዘግቡትን ዕድገትም የተነበየ ሲሆን 6 ነጥብ 2 በመቶ የዕድገት ትንበያን በማግኜት ሕንድ ቀዳሚውን ስፍራ መያዟንም ትንበያው አመላክቷል።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም(አይ.ኤም.ኤፍ) ባወጣው አዲስ የኢኮኖሚ የትንበያ ሪፖርት መሠረት የዓለም ኢኮኖሚ በ2025 ከነበረበት 3 ነጥብ 2 በመቶ ዕድገት በ2026 ወደ 3 ነጥብ 1 በመቶ ዝቅ እንደሚል ገልጿል።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም(አይ.ኤም.ኤፍ) ሀገራት በ2026 የሚያስመዘግቡትን ዕድገትም ተንብይዋል።

በዚህም በ2026 ዕድገት ከሚያስመዘግቡ ሀገራት መካከል እያደጉ ያሉ ገበያዎች እና ኢኮኖሚዎች በሚል ምድብ ውስጥ 6 ነጥብ 2 በመቶ የዕድገት ትንበያን በማግኜት ሕንድ ቀዳሚውን ስፍራ ይዛለች።

እንደቀጠና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ታዳጊ ሀገራት 5 በመቶ ዕድገት ያስመዘግባሉ በሚል በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጡ ሲሆን በዚሁ ምድብ ውስጥ እንደ ቀጠና አዳዲስ ወደዕድገት እየመጡ ያሉና በማደግ ላይ ያሉ የእስያ ሀገራት 4 ነጥብ 7 ዕድገት ያስመዘግባሉ በሚል በሦስተኛ ደረጃ ተቀምጠዋል።

እያደጉ ያሉ ገበያዎች እና ኢኮኖሚዎች በሚለው በዚህ ምድብ ውስጥ ከአፍሪካ እንደቀጠና ከሳሃራ በታች የሚለው የገባ ሲሆን እንደሀገር ደግሞ ሁለት ሀገራት፤ ናይጀሪያና ደቡብ አፍሪካ ብቻ ተካተዋል።

በዚህም በ2026 ናይጀሪያ 4 ነጥብ 2 ዕድገት እንደምታስመዘግብ የተተነበየ ሲሆን ይህም በምድቡ ውስጥ ከእስያ ቀጠና አቻዋ ቻይና ጋር እኩል ዕድገት የምታስመዘግብ ሀገር ያደርጋታል።

ባደጉ ሀገራት ምድብ ውስጥ የምትገኘኔው ጃፓን በ 0 ነጥብ 6 የዕድገት ትንበያ በ2026 ዝቅተኛ ዕድገት ከሚያስመዘግቡ ሀገራት መካከል የመጀመሪያውን ደረጃ ስትይዝ፤ በዚሁ ምድብ ውስጥ የምእገኜው ጣሊያን 0 ነጥብ 7፤ በዚሁ ምድብ ውስጥ የሚገኙት ፈረንሳይና ጀርመን እያንዳንዳቸው 0 ነጥብ 9 በመቶ ዕድገት ያስመዘግባሉ በሚል ዝቅተኛ ዕድገት ከሚያስመዘግቡት ውስጥ ተካተዋል።

አዲስ_ማለዳ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

BYD ከ115,000 በላይ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ላይ ማሻሻያ እንደሚያስፈልጋቸው ገለጸ

የቻይናው ግዙፉ የኤሌትሪክ መኪኖች አምራች ቢ.ዋይ.ዲ በዲዛይንና በባትሪ ተከላ...

የትራምፕን ንግግር የህንድ መንግስት ስለ ጉዳዩ ምንም የማዉቀዉ ነገር የለም ብሏል

የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የሩሲያን ነዳጅ ላለመግዛት መስማማታቸውን...

አቶ አህመድ ሽዴ ከእንግሊዝ የዓለም አቀፉ የልማት እና የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከእንግሊዝ የአለም አቀፍ የልማት...